በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA) በትውልድ አካባቢያችን ብሎም በአገራችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የጤናና የኢኮኖሚ መቃወስ ውስጥ ሊገቡ ለሚችሉ ወገኖቻችን ድጋፍ እንዲሆን የገንዘብ መዋጮ ስንሰብስብ መቆየታችን ይታወሳል።
የተሰበሰበውን ገንዘብ ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች ወደ ወላይታ ለማስተላለፍ ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን እያለ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአገራችን በተነሳው የጸጥታ ችግር እና የኮሚዩኒኬሽን መቋረጥ በተለይ የስምምነት ዶኩሜንቶችን መለዋወጥ የማያስችል ሆኖ ገንዘቡን በመላክ ለተረጂው ወገን የማዋል ሒደቱ ተስተጓጉሎ ቆይቶአል።
በአሁኑ ሰዓት ግን ነገሮች በተሻለ ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው ከተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መገናኘት በመቻሉ የአዋና አመራር በጁላይ 26, 2020 ባደረገው ስብሰባ በፕሮጀክት ንድፈ ሀሳብ ላይ ተነጋግሮ ወደ ውሳኔ ሀሳብ ደርሷል። ይህ የውሳኔ ሀሳብ ሥራ ላይ ከመዋሉና ሕጋዊ የስምምነት ሰነድ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ከመፈራረማችን በፊት የገንዘብ ድጋፍ ካደረጉ ወገኖቻችን አስተያየት/feedback እንዲሰጠን ዝርዝር ማስታወሻ GoFundMe በኩል የተላከላችሁ በመሆኑ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ ይህን ተከትላችሁ አስተያየታችሁን እንድትሰጡን በአክብሮት እናሳስባለን።
እግዚአብሔር አገራችንንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!
AWANA

AWANA