“የመማር ማስተማር ሥራዎችን ለማሳለጥ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው” ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ
ዳሞት ወይዴ፤ መስከረም 25/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ዳጋጋ ሌንዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት 6 አዳድስ ክፍሎች ግንባታና ያረጁ ክፍሎች ጥገና በ(AWANA) በአሜሪካ ያሉት ወላይታ ተወላጆች የተገነባው ት/ት ቤት ተመርቋል ።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በፕሮግራሙ ባስተላለፉት መልዕክት የዞናችንን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት በማሳደግ ረገድ የድርሻውን እንደሚያበረክት ለሚታመነው በውድ ልጆቻችን ከአሜሪካን ሀገር መጥቶ በትዉልድ ቀያቸዉ ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃታቸውን አመስግነዋል ።
የአንድ ሀገር ልማትና እድገት መሠረቱ ትምህርት በመሆኑ ለትምህርት ጥራት ሁሉም ባለድርሻ የበኩሉን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በሀገራችን ብሎም በዞናችን የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ስሰሩ ቆይተዋል፡፡
ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ የትምህርት ስብራት ለመጠገን እንደሚሠራ ጠቁመዋል ፡፡
በትምህርት ውጤት ላይ ለታየው ስብራት ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የፖለቲካ አመራሩ፣ የትምህርት ባለሙያዎችና ወላጆች ሁሉም የየራሱ አሻራ ያለዉ በመሆኑ ስብራቱን ለመጠገንና ትዉልዱን ለመካስ ወስኖ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
መንግሥት ስብራቱን ለመጠገን ፖሊሲዎችን በመቅረጽና የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ፡፡
የትምህርት መሰረተ ልማትን በሟሟላት ትምህርት ቤቶችን የማገዝ ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የትምህርት ሪፎርም የተካሄደባቸዉ ዘርፎች ካሪኩለም መቀየር፣ የመምህራንን አቅም መገንባት፣ የትምህርት ሥርዓት አስተዳደር ማሻሻል እና መቀየር፣ መሠረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የፈተና ሥርዓቱን ማሻሻል፣ የተማሪዎችን ምገባ መጀመር እና በከፍተኛ ትምህርት ጥራት ላይ መሥራት ይገበዋል ብለዋል፡፡
የትምህርት ሪፎርሙን አጠናክረን ካልሠራን፣ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አይጠገንም፤ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠልን የምናስበውን ዕድገት እና ብልጽግና ልናመጣ እንደማይቻል አስረድተዋል ::
ስለዚህም በዞናችን በልዩ ተነሳሽነት የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት በሁሉም የዞናችን አከባቢዎች እንድገነባና ህፃናት ከታች ጀምሮ በቂ ትምህርት እያገኙ እንድያድጉ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰር ዳታ ዴአ የ(AWANA) አዋና ፕረዚዳንት በቪዲዮ ከሰሜን አሜርካ ባስተላለፉት መልዕክት ለወላይታ አከባቢ በተቻለን መጠን በመንግሥት ጎን በመሆን ለሕዝብ በተለያዩ ዘርፍ ለመደገፍ እንደሚሠሩ ተናግረዋል ።
ከዚህም ባሻገር የትምህርት መሠረተ ልማት የማሟላቱ ስራ እየተሰራ ያለ ቢሆንም ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለመፍጠር በመንግስት ጎን በመቆም በእንደንዝህ መልኩ የሚደረጉ ድጋፎች የዞናችን መንግስት ከፍተኛ ዕዉቅና ይሰጣል ብለዋል፡፡
ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሚሆነዉ ይህ ት/ቤት ተማሪዎችን በዕዉቀት በመገንባት ለዞናችን ብሎም ለሀገራችን ዉሌታ እንደሚዉል አልጠራጠርም፡፡
አቶ ተክሌ ቶማ የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ትምህርት ቤቱ ለአካባቢውን ማህበረሰብ የቅርብ ተደራሽ የመሆኑን ያህል ተማሪው ስብዕናው የተገነባ፣ የደረጃውን ክህሎትና ዕውቀት የታጠቀ፣ በራሱ የሚተማመን፣ ሀገርና ሰላም ወዳድ፣ ለቴክኖሎጂና ለስራ ፈጠራ ዝንባሌ ያለው ዜጋ ሆኖ እንዲያድግ የመማር ማስተማሩ ስራ ትኩረት እንደሚሰጥ ይጠበቃል ብለዋል ።
ለዳጋጋ ለንዳ ትምህርት ቤቱ አድስ ግንባታ ፣ የነባሩን ለመጠገንና በክፍሉ ቁሳቁስ ለማሟላት ከAWANA እንዲሁም ከግለሰቦችና ከኅብረተሰቡ ተሳትፎ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክሌ አብራርተዋል ።
በምረቃው ፕሮግራም የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ ም/አስተዳዳሪ አቶ ተሰፋሁን ታዲዎስ ፣ የወላይታ ዞን ረዳት መንግሥት ተጠሪ አቶ መስፍን ቶማስ ፣ ጨምሮ የዞኑና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና የAWANA አስተባበሪዎች፣ የትምህርት ማህበረሰብ ተሳትፈዋል ።




AWANA