AWANA

News/Blogs

Awana Wolaita at a Glance: Success in Education and Community Development (2025)

Awana Wolayti Luxettaaninne Deretetta Dichchan 2018 ML Ottido Oosota xeelliyaagaan kaalidi de’iya YouTube be’anaw shoobettideta: https://youtu.be/Vv956eBgRVwበ2018 ዓ.ም. አዋና ወላይታ በትምህርትና በማህበረሰብ እድገት ያከናወነዉን ትልቅ ስኬት ለማየት ከታች ያለውን የYouTube ቪዲዮ ይመልከቱ።Watch the following YouTube video to see Awana Wolaita’s 2025 achievements in education and community development in Wolaita.

በ AWANA – Association of Wolaita’s and Allies in North America የተገነባው ት/ት ቤት ተመርቋል

“የመማር ማስተማር ሥራዎችን ለማሳለጥ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው” ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ዳሞት ወይዴ፤ መስከረም 25/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ዳጋጋ ሌንዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት 6 አዳድስ ክፍሎች ግንባታና ያረጁ ክፍሎች ጥገና በ(AWANA) በአሜሪካ ያሉት ወላይታ ተወላጆች የተገነባው ት/ት ቤት ተመርቋል ። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ…

በወላይታ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የመብት ጥሰትና አፈናን በተመለከተ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA) እና በዋሽንግተ ዲሲ አካባቢ የወላይታ ኅብረት (WCDC) በጋራAugust 9, 2022 ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው የወላይታ ብሔር በኢትዮጵያ ታሪክና አገር ግንባታ ሂደት ከሌሎች የአገራችን ህዝቦች ጋር ኢትዮጵያን በማልማት፣ አንድነቷንና ሉአላዊነቷን በማስከበር ረገድ የሕይወት መሥዋዕትነት ሁሉ እየከፈለ የኖረ ኩሩና አገር ወዳድ ሕዝብ መሆኑን ማንም አይክደውም። አገራችንን ከፀረ-ሠላም ኃይሎች ለመታደግ እንዲሁም…

Awana Wolaita at a Glance: Success in Education and Community Development (2025)

Awana Wolayti Luxettaaninne Deretetta Dichchan 2018 ML Ottido Oosota xeelliyaagaan kaalidi de’iya YouTube be’anaw shoobettideta: https://youtu.be/Vv956eBgRVw
በ2018 ዓ.ም. አዋና ወላይታ በትምህርትና በማህበረሰብ እድገት ያከናወነዉን ትልቅ ስኬት ለማየት ከታች ያለውን የYouTube ቪዲዮ ይመልከቱ።
Watch the following YouTube video to see Awana Wolaita’s 2025 achievements in education and community development in Wolaita.

በ AWANA – Association of Wolaita’s and Allies in North America የተገነባው ት/ት ቤት ተመርቋል

“የመማር ማስተማር ሥራዎችን ለማሳለጥ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው” ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ

ዳሞት ወይዴ፤ መስከረም 25/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ዳጋጋ ሌንዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት 6 አዳድስ ክፍሎች ግንባታና ያረጁ ክፍሎች ጥገና በ(AWANA) በአሜሪካ ያሉት ወላይታ ተወላጆች የተገነባው ት/ት ቤት ተመርቋል ።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በፕሮግራሙ ባስተላለፉት መልዕክት የዞናችንን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት በማሳደግ ረገድ የድርሻውን እንደሚያበረክት ለሚታመነው በውድ ልጆቻችን ከአሜሪካን ሀገር መጥቶ በትዉልድ ቀያቸዉ ገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃታቸውን አመስግነዋል ።

የአንድ ሀገር ልማትና እድገት መሠረቱ ትምህርት በመሆኑ ለትምህርት ጥራት ሁሉም ባለድርሻ የበኩሉን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሀገራችን ብሎም በዞናችን የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ስሰሩ ቆይተዋል፡፡

ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ የትምህርት ስብራት ለመጠገን እንደሚሠራ ጠቁመዋል ፡፡

በትምህርት ውጤት ላይ ለታየው ስብራት ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የፖለቲካ አመራሩ፣ የትምህርት ባለሙያዎችና ወላጆች ሁሉም የየራሱ አሻራ ያለዉ በመሆኑ ስብራቱን ለመጠገንና ትዉልዱን ለመካስ ወስኖ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

መንግሥት ስብራቱን ለመጠገን ፖሊሲዎችን በመቅረጽና የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ፡፡

የትምህርት መሰረተ ልማትን በሟሟላት ትምህርት ቤቶችን የማገዝ ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የትምህርት ሪፎርም የተካሄደባቸዉ ዘርፎች ካሪኩለም መቀየር፣ የመምህራንን አቅም መገንባት፣ የትምህርት ሥርዓት አስተዳደር ማሻሻል እና መቀየር፣ መሠረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የፈተና ሥርዓቱን ማሻሻል፣ የተማሪዎችን ምገባ መጀመር እና በከፍተኛ ትምህርት ጥራት ላይ መሥራት ይገበዋል ብለዋል፡፡

የትምህርት ሪፎርሙን አጠናክረን ካልሠራን፣ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት አይጠገንም፤ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠልን የምናስበውን ዕድገት እና ብልጽግና ልናመጣ እንደማይቻል አስረድተዋል ::

ስለዚህም በዞናችን በልዩ ተነሳሽነት የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት በሁሉም የዞናችን አከባቢዎች እንድገነባና ህፃናት ከታች ጀምሮ በቂ ትምህርት እያገኙ እንድያድጉ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ዳታ ዴአ የ(AWANA) አዋና ፕረዚዳንት በቪዲዮ ከሰሜን አሜርካ ባስተላለፉት መልዕክት ለወላይታ አከባቢ በተቻለን መጠን በመንግሥት ጎን በመሆን ለሕዝብ በተለያዩ ዘርፍ ለመደገፍ እንደሚሠሩ ተናግረዋል ።

ከዚህም ባሻገር የትምህርት መሠረተ ልማት የማሟላቱ ስራ እየተሰራ ያለ ቢሆንም ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለመፍጠር በመንግስት ጎን በመቆም በእንደንዝህ መልኩ የሚደረጉ ድጋፎች የዞናችን መንግስት ከፍተኛ ዕዉቅና ይሰጣል ብለዋል፡፡

ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሚሆነዉ ይህ ት/ቤት ተማሪዎችን በዕዉቀት በመገንባት ለዞናችን ብሎም ለሀገራችን ዉሌታ እንደሚዉል አልጠራጠርም፡፡

አቶ ተክሌ ቶማ የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ትምህርት ቤቱ ለአካባቢውን ማህበረሰብ የቅርብ ተደራሽ የመሆኑን ያህል ተማሪው ስብዕናው የተገነባ፣ የደረጃውን ክህሎትና ዕውቀት የታጠቀ፣ በራሱ የሚተማመን፣ ሀገርና ሰላም ወዳድ፣ ለቴክኖሎጂና ለስራ ፈጠራ ዝንባሌ ያለው ዜጋ ሆኖ እንዲያድግ የመማር ማስተማሩ ስራ ትኩረት እንደሚሰጥ ይጠበቃል ብለዋል ።

ለዳጋጋ ለንዳ ትምህርት ቤቱ አድስ ግንባታ ፣ የነባሩን ለመጠገንና በክፍሉ ቁሳቁስ ለማሟላት ከAWANA እንዲሁም ከግለሰቦችና ከኅብረተሰቡ ተሳትፎ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክሌ አብራርተዋል ።

በምረቃው ፕሮግራም የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ ም/አስተዳዳሪ አቶ ተሰፋሁን ታዲዎስ ፣ የወላይታ ዞን ረዳት መንግሥት ተጠሪ አቶ መስፍን ቶማስ ፣ ጨምሮ የዞኑና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና የAWANA አስተባበሪዎች፣ የትምህርት ማህበረሰብ ተሳትፈዋል ።

በወላይታ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የመብት ጥሰትና አፈናን በተመለከተ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA) እና በዋሽንግተ ዲሲ አካባቢ የወላይታ ኅብረት (WCDC) በጋራ
August 9, 2022

ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው የወላይታ ብሔር በኢትዮጵያ ታሪክና አገር ግንባታ ሂደት ከሌሎች የአገራችን ህዝቦች ጋር ኢትዮጵያን በማልማት፣ አንድነቷንና ሉአላዊነቷን በማስከበር ረገድ የሕይወት መሥዋዕትነት ሁሉ እየከፈለ የኖረ ኩሩና አገር ወዳድ ሕዝብ መሆኑን ማንም አይክደውም።

አገራችንን ከፀረ-ሠላም ኃይሎች ለመታደግ እንዲሁም ሠላሟንና ጸጥታዋን ለማስከበር በሚደረገው ጥረት የወላይታ ሕዝብ ገንዘቡንና ጊዜውን ብቻ ሳይሆን የልጆቹንም ደም የገበረ የአገርን መደፈር አጥብቆ የሚጠላ ብርቱ ሕዝብ መሆኑን ማስረዳትም አያስፈልግም።

ሆኖም ግን በየዘመናቱ የተነሱት የኢትዮጵያ ገዢዎች ለህዝቡ የሚመጥን ሥርዓት ከመዘርጋት ይልቅ በተቃራኒው አስተዳደራዊና መዋቅራዊ በደልና ጭቆና ሲያፈራርቁበት ኖረዋል። በዚህም ምክንያት በነፃነትና እኩልነት ለመኖርና ለመዳኘት የነበረው የሕዝብ ፍላጎት እስከ ዛሬ መክኖ ቀርቶአል። ለዚህ ብዙ ማሳያዎች አሉ።

ለምሳሌ ያህል:- ሕወኃት በምትመራው የኢህአዴግ ዘመን የወላይታንና የአካባቢውን ሕዝብ ባሕልና ቋንቋ፣ የአኗኗር ወጉንና ሥርዓቱን ከምድር ገጽ ለማጥፋት ታቅዶ ለግል ጥቅማቸውና ሥልጣናቸው ቅድሚያ የሚሰጡ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የወላይታ ተወላጆችም ጭምር በመጠቀም በየትኛውም ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አፋኙ መንግሥት ሕዝቡን መግቢያ መውጫ አሳጥቶ የብዙዎችን ደም አፍስሶና በርካታዎችን አስሮና ከቤት ከንብረቱ አፈናቅሎ የነበረ ቢሆንም በወላይታ ሕዝብ ቁርጠኛ ትግል ጥረቱ መቀልበሱ የሕዝባችን የቅርብ ጊዜ ትዝታው ነው።

“ወጋጎዳ” የተባለውን ድብልቅ ባሕልና ቋንቋ በሕዝብ ላይ በመጫን የአካባቢውን ማኅበረሰብ ያስቆጡት፣ ኢፍትሓዊ ድርጊት በሕዝቡ ላይ የፈጸሙት የጊዜው ካድሬዎች ለፍትሕ ሳይቀርቡ፣ በገዛ ወገናቸው ላይ ላደረሱት በደልና ግፍ ሳይጠየቁ የታለፉ ከመሆናቸውም በላይ በተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች እስከ ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት ሥልጣን ተሹመው የነበረ መሆኑም አይዘነጋም። ያንን ሁሉ ድርጊት በሕዝባችን ላይ የፈጸሙት ግፈኞች በተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ ተሰግስገው ሕዝባችንን አሳር ሲያበሉ የኖሩ ሲሆን ለዛሬውም የሕዝባችን መከራ እጃቸው እንዳለበት ይታመናል።

ከአንድ ዓመት በፊት ብልጽግና በሚመራው የለውጥ መንግሥት ደግሞ “የክልል ጥያቄ አጥብቃችሁ ለምን ትጠይቃላችሁ?” በሚል ምክንያት ብቻ በሶዶ እና በቦዲቲ ከተሞች በንጹኃን ዜጎች ላይ ከፌደራልና ከደቡብ ክልል መንግሥታት በተላኩ ታጣቂዎች የዘነበባቸው ጥይት የብዙዎችን ሕይወት ቀጥፎአል። ለዕለት ጉዳያቸው ወጥተው መንገድ ዳር የነበሩ እርጉዝ ሴትን ጨምሮ በርካታ ሕጻናትና ሰላማዊ ሰዎች በዚሁ ወቅት በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የወላይታ ሕዝብ እንደሌሎቹም የአገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ሕገ መንግሥቱ ያጎናጸፈውን ራስን በራስ የማስተዳደር ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመጠቀም በማያወላዳ አቋም ክልል የመሆን ጥያቄ አቅርቦ በዞኑ ምክር ቤት አስወስኖ እስከ ፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርቦ ምላሽ ሲጠባበቅ ቆይቶአል። ይህንን ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄውን ሕዝቡ በሠለጠነና ፍጹም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ሲጠይቅ የነበረ ቢሆንም በመንግሥት በኩል የተለያዩ ትንኮሳዎች ሲደርሱበት እንደነበር ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው። የወላይታ ሕዝብ በሌሎች አካባቢዎች እንደታየው የሌላ አካባቢ ተወላጆችን ያሸማቀቀበት፣ ብሔር ለይቶ ያፈናቀለበት ያሳደደበት፣ የገደለበት ቀን ያልነበረ መሆኑ ለዚህ ማሳያ ነው።

በአሁኑ ጊዜ የወላይታ ሕዝብ እየጠበቀ የሚገኘው የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ሆኖ ሳለ የሕዝቡን ፍላጎት ወደ ጎን በመተው ለመረዳት በሚከብድ ፍጥነትና አኳኋን በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ውሳኔ ሰጪነት ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ውሳኔ ተደርጎ ለፌደሬሽን ምክር ቤት መቅረቡ ተሰምቶአል። ይህ ሕዝቡን ያፈነና የብልጽግና ካድሬዎች እንጂ የሕዝቡን ይሁንታ ያላገኘ ውሳኔ ተመሳሳይ ሥነ ልቦና አላቸው ከሚባሉት ሕዝቦች ጋር ለመጨፍለቅ ብርቱ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

ይህም አሠራር “አለባብሶ ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” ዓይነት ከመሆኑም በላይ ይኼኛው መንግሥት ካለፉት መንግሥታት ስሕተቶች ምንም ትምህርት ያላገኘ መሆኑን አመላካች ነው። ይህ አፋኝ ውሳኔ የወላይታን ሕዝብ መብትና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የአካባቢውን ሕዝቦች ጥያቄና ፍላጎት የገፋ መሆኑ ግልጽ ነው።

በመሆኑም እኛ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የወላይታ ተወላጅ ዲያስፖራ አባላት የወላይታ ሕዝብ ሕግንና ሥርዓትን ተከትሎ ያቀረበውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለማዳፈን የሚደረገውን መንግሥታዊ አፈና በተመለከተ በሁለቱ ድርጅቶች በኩል ከዚህ በታች ያለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

  1. የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ ሕገ-መንግሥታዊ የክልልነት አደረጃጀት ሆኖ ሳለ ሕገ መንግሥቱ የማያውቀውን “ክላስተር” የተባለውን አደረጃጀት በማምጣት የሕዝቡን ፍላጎት ለማፈን ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ውስጥ የተገባበት ሁኔታ በወላይታ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እየገለጽን በካድሬ የተፈበረከው “ክላስተር” የተባለው መዋቅር ኢሕገ-መንግሥታዊ በመሆኑ ይህንን ድርጊት የሚፈጽመው አካል በሕዝብም በታሪክም የሚጠየቅ መሆኑን አውቆ ከዚህ የጥፋት መንገዱ እንዲመለስ እናሳስባለን።
  2. የወላይታ ሕዝብ ይህንን የክልልነት ጥያቄውን በየቀበሌያትና በየወረዳዎች ሁሉ አስወስኖ በስተመጨረሻም በዞን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ ጸድቆ ለደቡብ ክልልና ለፌደሬሽን ምክር ቤት የተላከ ሕዝባዊና ሕጋዊ ውሳኔ ወደ ጎን ተደርጎ በአሁኑ ጊዜ ከላይ ወደታች አዲስና አስደንጋጭ ውሳኔ በሕዝቡ ላይ መጫን የሕዝቡን ሉዓላዊነትና ሕጋዊ መብት መጋፋት መሆኑ ታውቆ ሂደቱ እንዲቋረጥ እናሳስባለን።
  3. የወላይታ ሕዝብ በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች በመሳተፍ የበኩሉን ኃላፊነትና ግዴታውን እንዲወጣ የሚጠበቅበትን ያህል እንደ ዜጋ የሚጠይቃቸውን ሕጋዊ መብቶችን ተጠቃሚ እንዳይሆን የሚደረገውን የትኛውንም የገዢውን ፓርቲና መንግሥት መዋቅራዊ አፈና እንቃወማለን።
  4. የወላይታ ሕዝብ ይህንን የመብት ጥያቄውን እንዲያቆም ለማድረግ ከየአቅጣጫው የሚነዙትን የማሸማቀቂያ ዘዴዎችን “ክልል መጠየቅ ዘረኝነት ነው”፣ “ጠባብነት ነው”፣ “ጎጠኝነት ነው መታጠር ነው”፣ “ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው” የሚሉትና ሌሎችንም አጓጉል ትርጓሜዎችና አባባሎች ጊዜ ያለፈባቸው ስልቶች መሆናቸው ታውቆ እንዲቆሙ እናሳስባለን።
  5. በተለያዩ የአገራችን ክልሎች ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ፣ በየዕለቱ እንደ በግ ሲታረዱ፣ በገዛ አገራቸውም የመኖር መብታቸውን ሲገፈፉ፣ መከላከልና ሕጋዊ ከለላ ሊሰጥ ያልቻለ ብልጽግና መራሹ መንግሥት ፍጹም ሠላማዊ የሆነውን ሌሎችንም ወንድም ኢትዮጵያውያንን አቅፎ የተቀመጠውን ሕዝብ ከማሸበር ተግባሩ እንዲቆጠብ እናሳስባለን።
  6. እየፈረሰ የሚገኘው የደቡብ ክልል መንግሥት ትክክለኛውን የሕዝብ ጥያቄ ወደ ጎን በማድረግ “በሳይንሳዊ ጥናት እናዋቅራለን” ሲል ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ በክላስተር እናደራጃለን በሚል ውሳኔ ከተሞችን እንደዚህና እንደዚያ እናደርጋለን በሚል መደለያ ጭምር ለዘመናት በመተሳሰብና በአጋርነት የኖረውን አጎራባች ሕዝብ እርስ በርሱ ለማጋጨት ከሚያደርገው ኃላፊነት ከጎደለው ተግባሩ እንዲቆጠብ እናሳስባለን።
  7. በመጨረሻም ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ የጠየቀው መሰረታዊ የመብትና የእኩልነት ጥያቄ በፍትሃዊ መንገድና በእዉነተኛ መግባባት እስካልተፈታ ድረስ አከባቢው ላልተቋረጠ የመብት ትግል ውጥረትና ቀውስ የሚያጋልጥ በመሆኑ በፍትዊነትና እኩልነት የሚያምን ሃገር ወዳድ ኢትዮዽያዊ ሁሉ ሊያሳስብ የሚገባና የሚወገዝ ተግባር መሆኑንም እናሳስባለን።

“I am Wolayta”: Taani Wolayta book authored by Mrs. Manyahilishal Madebo is now available on Amazon, Barnesandnoble, Walmart and other online stores

This Book titled “I am Wolayta”: Taani Wolayta authored by USA based Mrs. Manyahilishal Madebo is now available online and it covers fascinating stories about Wolayta culture, social life, childhood experiences and other details, especially for Children who want to know the everyday life of Wolayta’s kids in Wolayta, Ethiopia.
As you read, five senses activate remembering the aroma of the food cooked during traditional holidays in Wolayta and other amazing Childhood memories. For those who live outside of Wolayta and want to teach their kids about Wolayta culture and childhood experiences, this is perfect Book.

God Bless Wolayta, Ethiopia!!!

This Book can be ordered from the below web stores:

https://www.amazon.com/I-am-Wolayta-Tanni/dp/1662921217 ,
https://www.barnesandnoble.com/w/i-am-wolayta-manyahilishal-dado/1141052173 , https://www.walmart.com/ip/I-am-Wolayta-Tanni-Wolayta-Hardcover-9781662921216/696148504?wmlspartner=wlpa&selectedSellerId=0

AWANA COVID-19 Funding and other support to Wolayta, Ethiopia as per WOLAYTA TV

AWANA COVID-19 Funding and other support to Wolayta, Ethiopia as per WOLAYTA TV

Upcoming AWANA Meeting

Gentle reminder of tomorrow’s meeting and some pictures from our visit to Ethiopia including Wolaita, Ethiopia in January 2022. More to be shared in the tomorrow meeting (2/12/2022)

ማስታወቂያ ለመላው የAWANA አባሎችና ወዳጆች:-

ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ Feb. 12, 2022 በዲሲ ሰዓት ልክ 8:00PM ላይ በሚኖረን በZoom በምናደርገው ስብሰባ ላይ የማኅበራችን ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዳታ ዴኣን ጨምሮ ሌሎችም ተወካዮቻችን ከአገር ቤት ጉብኝት መልስ የሚያቀርቡልንን ሪፖርት የምናደምጥበት፣ በአንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር የምናደርግበት፣ እንዲሁም ደግሞ በማኅበሩ የወደፊት የሥራ ሒደት ላይ የምንወያይበት ጊዜ በመሆኑ በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር አባላትና ሌሎችም ደጋፊዎች ሁላችሁም እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት እየጋበዝን የZoom ሊንኩን ቀኑ ስቃረብ የምናስታውቃችሁ መሆኑንም እንገልጻለን።መልካም ሳምንት!!

የAWANA ሥራ አስፈጻሚ

ጉዳዩ:- የኢሳት ጋዜጠኛ አቶ ግዛው ስለ ወላይታ የሰጠውን ጥላቻ የተሞላበትን አስተያየት ይመለከታል። September 16,2021

በመስከረም 3 ቀን 2014 ዓ.ም አቶ መሳይ መኮንን ይመራ በነበረው “ዕለታዊ” በተሰኘው የኢሳት መርሃ ግብር ላይ ስለ ብሔርተኝነት በተነሳው ሐሳብ አቶ ግዛው ለገሰ ስለ ወላይታ ብሔርተኝነት ማቆጥቆጥ አስታውሰው መጥፋትና መሸነፍ ያለበት መሆኑን መናገራቸው በወላይታ ሕዝብ ዘንድ ቅሬታ፣ ጥያቄና ቁጣን የጫረ ተግባር ሆኗል።

ከኢሳት ስቱዲዮ ካሁን ቀደምም እንዲህ ዓይነት የወላይታን ሕዝብ ዒላማ ያደረጉ ሕዝቡን ከሌላ ወንድም ሕዝብ ጋርና ከመንግሥት ጋር ለማጋጨት ሆን ተብለው የተሸረቡ የሚመስሉ ዝግጅቶች አየር ላይ ሲውሉ የነበረበትንም ሁኔታ የምንዘነጋው አይደለም።

የወላይታ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመሆን የአገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስጠበቅ እንደ ሁል ጊዜውም የሕይወት መስዋዕትነትን ጨምሮ የትኛውንም ዋጋ እየከፈለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነት በሬ ወለደ ክስ በመላው የወላይታ ሕዝብ ላይ ማንሳት “ሠላም ወዳድ ነኝ የአገርን አንድነት እፈልጋለሁ” ከሚሉ ግለሰቦች ኢሳትን በሚመስል ታዋቂ ሚዲያ አማካይነት መለቀቁ በእውነቱ የሚያስተዛዝብና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው።

የወላይታ ሕዝብ የኢትዮጵያን አንድነት ሊፈታተን በሚችል መልኩ አክራሪ ብሔርተኞች በሚሸርቡት ሴራ ለአንድ አፍታም ሳይወዛገብ ለኢትዮጵያዊነትና ለሕብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም በመታመን አሁን ሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት በሚፈቅደው መሠረት የመደራጀትና የመልማት መብቱን መጠየቁ የታወቀ ነው። ይህም እየሆነ ያለው የወላይታ ብሔር እንደ ሌሎቹ የአገራችን ብሔሮች የራሱን ባሕል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ የማሳደግ ተፈጥሮአዊ መብት ለመጠቀም ሲል መሆኑም መታወቅ አለበት። ይህ መብቱ እንዳይከበርለት የሚደረገውን የትኛውንም ሥነ ልቦናዊና አካላዊ ጥቃት የማንቀበለው መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ መግለጽ እንወዳለን።

አቶ ግዛው ለገሰ ያለ ምንም በቂ ማስረጃ የጋዜጠኝነትንም ሥነ ምግባር በማይመጥን መልኩ እንዲህ ያለ ግብረ ገብነት የሌለውን ንግግር በመላው የወላይታ ብሔር ላይ በመናገሩ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር ቅሬታውን በፕሬዚዳንቱ አማካይነት በሕጋዊ ደብዳቤ ለኢሳት ቢሮ በማድረስ ምላሹን እየተጠባበቀ የሚገኝ መሆኑንም ለማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎች መግለጽ እንወዳለን።

የኢሳት ቢሮ እንዲህ ያሉ የሕዝብን ቁጣ የሚያነሳሱ፣ መንግሥትንም በሕዝብ ላይ ያለ አግባብ ሊቀሰቅሱ የሚችሉ የሽብር ተግባራትን የሚፈጽሙ ጋዜጠኞችን የማረም እርምጃ በመውሰድ ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ ያደርጋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። የድርጊቱ ፈጻሚውም ሆነ ሚዲያው ክቡር በሆነው የወላይታ ሕዝብ ላይ ያለአግባብ የተደረገውን ዘመቻ በሚመለከት ግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቅ በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (Awana Wolayta) ያሳስባል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

መልካም አዲስ ዓመት!!

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA – Wolayta)

Wolaita Dichchanaw Amoy de’iyo Ubbay AWANA qaatuwan AWANA gadawata demmanaw pengge dooya!

AWANA eqotay Wolaita diaspora issippe shishshiyoogan dumma dumma dichcha baasotun Wolaita motta madiddi de’iyooge erettes. Payatettan, Luxettan, daro dichcha hillatun AWANA ra gidiyoogan WOLAITA deriya maddanaw koyyiya oonikka AWANA websiteyan allalliya poliya gadawata demmana mala bonchchuwan Shobetideta.

ኢትዮጵያ በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቀቀች / ነሃሴ 2/2013

ኢትዮጵያ በ2020 ቶኪዮ ኢሊምፒክ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቃለች።የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች ፍጻሜውን ያገኛል።ኢትዮጵያም በአትሌቲክስ፣ በሴቶች ብስክሌት፣ በውሃ ዋና እና በወንዶች ወርልድ ቴኳንዶ የውድድር አይነቶች የተካፈለች ሲሆን፤ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቃለች።በውድድሩም 37 ኢትዮጵያውን አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል በሴቶች ብስክሌት፣ በወንዶች ውሃ ዋና፣ እንዲሁም በወንዶች ወርልድ ቴኳንዶ በእያንዳንዳቸው አንድ አንድ አትሌቶች ተካፍለዋል።ኢትዮጵያ በውድድሩ በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አማካኝነት በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም በአትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር ወንዶች መሰናክል መድድር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።በአትሌት ለተሰንበት ግደይ አማካኝነት በሴቶች በ10 ሺህ ሜትር እንዲሁም በአትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድሮች የነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ከተሳተፉ 200 በላይ ሀገራት መካከል 86ቱ የሜዳሊያ ሰንጠረዡ ውስጥ መግባት የቻሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በአንድ ወርቅ፣ አንድ ብርና በሁለት ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።አሜሪካ 39 የወርቅ፣ 40 ብርና 33 ነሐስ ሜዳሊያ ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች።ቻይና በ38 ወርቅ ፣31 ብርና 18 የነሐስ ሜዳሊያ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ፤ አዘጋጇ ጃፓን 27 ወርቅ ፣14 ብርና 17 ነሐስ ሜዳሊያ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።አፍሪካዊቷ ኬኒያ በአራት ወርቅ አራት ብርና ሁለት ነሐስ ሜዳሊያ በመሰብሰብ በውድድሩ ከተካፈሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ስትሆን፤ ከዓለም 19ኛ ደረጃን ማግኘት ችላለች።ዪጋንዳ በሁለት ወርቅ ፣አንድ ብርና አንድ ነሐስ ከዓለም 36ኛ፤ ከአፍሪካ ሁለተኛ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ በአንድ ወርቅና ሁለት ብርከ ዓለም 52ኛ ከአፍሪካ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።ግብጽ በአንድ ወርቅ፣ አንድ ብርና አራት ነሀስ ከዓለም 54ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 4ኛ ደረጃን ይዛለች።ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ አትሌቶችን ያሳተፈች ቢሆንም፤ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር ከ1996 የአትላንታ ኦሊምፒክ በኋላ ዝቅተኛ የሚባል ውጤት የተመዘገበበት ሆኗል። (ኢዜአ)