AWANA

በወቅታዊ የወላይታ ዞን ጉዳይ ላይ የሚደረግ ውይይት August 2020

በወላይታ ሕዝብ ላይ መንግሥት እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃና መሠረታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር-AWANA Date: 8/11/2020

በወላይታ ሕዝብ ላይ መንግሥት እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃና መሠረታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር-AWANA 8/11/2020
******************************************************
ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ መንግሥት በወላይታ ሠላማዊ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃና እሱንም ተከትሎ የፈሰሰውን የንጹኃን ወላይታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በግፍ መገደል በታላቅ ሐዘንና የልብ ስብራት እየተከታተልን ነው። በወላይታ ሕዝብ ላይ ይህ አስደንጋጭ የግፍ እርምጃ እየተወሰደበት ያለው በክልል ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር መዋቅራዊ ጥያቄ መሆኑ ይታወቃል። የወላይታ ሕዝብ ይህንን ጥያቄ ካቀረበበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሠላማዊ በሆነ ሁኔታ ሲታገል መቆየቱ ይታወሳል። ሆኖም ግን መንግሥት በቸልተኝነት ሕግንና ሕጋዊነትን ባለማክበር ሕዝቡን ሲያፍን መቆየቱን በተግባር ሲያሳይ ቆይቶአል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ አንጻራዊ በሆነ ለውጥና ሽግግር ላይ ትገኛለች። የወላይታ ሕዝብ በዚህ የሽግግር ወቅት ብዙ ዋጋ የከፈለና ብዙም መከራ የተፈራረቀበት መሆኑ የሚታወስ ነው።

የወላይታ ሕዝብ ይህንን የክልልነት ጥያቄ ያነሳው በስሜታዊነት ተነሳስቶ ወይም የሌሎችን ፈለግ በመከተል ብቻ ወይም እንደሚባለው ከሌሎች ሀይሎች የተሰጠ የቤት ሥራ አድርጎ ሳይሆን በተደጋጋሚ የደረሰበትን አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ጭቆናና በደል ለመግፈፍ፣ ሕዝቡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር የልማት መሠረታዊ መብት ለመጠቀም፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ የደረሰበትን ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት (ሞት፣ መፈናቀል፣ በቁም ሰዎች የተቃጠሉበት፣ ሕጻናት በዱላ ተቀጥቅጠው የተገደሉበትና አስክሬናቸው በመሬት የተጎተተበት) ግፍና በደል መቃወምን መሠረት ያደረገ መሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያንና መላው ዓለም የታዘቡት ነው።

ይህንን ሠላማዊ የሕዝብ ጥያቄ ከተለያዩ የአገሪቱን ለውጥና ዕድገት ከማይፈልጉ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ድርጅቶች ጋር በማያያዝ መንግሥት እየሄደበት ያለውን አቅጣጫ እንዲያርም በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር አባላት በዛሬው ዕለት Aug 10,2020 ባደረግነው ጠቅላላ ጉባዔ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ባለ ስምንት ነጥብ መግለጫ አውጥተናል።

1. የወላይታ ሕዝብ ሕግንና ሕጋዊነትን ተከትሎ በሠላማዊ መንገድ ብቻ ጥያቄውን አቅርቦ በትዕግሥት እየተጠባበቀ ባለበት ሁኔታ በሕዝቡ ዘንድ ምንም ዓይነት አመጽ ሳይታይበት መንግሥት ሠላማዊ በሆኑ ዜጎች ላይ ሕጻናትን ጨምሮ በመግደል የከፈተውን አጠቃላይ የኃይልና የሽብር እርምጃ እያወገዝን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያቆም እንጠይቃለን።

2. በዚህ ሰብኣዊነት በጎደለውና አሰቃቂ ሁኔታ አካላቸውን ለተጎዱት ፈውስን፣ በጭካኔ ለተገደሉት እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን እየተማጸንን ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የወላይታ ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

3. ከተለያዩ ምንጮች እንደተሰማውና መንግሥትም እንደገለጠው በዚሁ ወቅት ታፍሰው የታሠሩ አካባቢውን እያስተዳደሩ የሚገኙ የሕዝብ መሪዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣ የኃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች፣ የወጣቱን ክንፍ የሚመሩት ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።

4. መንግሥት ማንኛውንም መሠረታዊና ወቅታዊ የሕዝብ ጥያቄ በኃይል እርምጃ ሳይሆን ከሕዝቡና ከሕዝቡ መሪዎች ጋር በቅርበት በመመካከር ፍትሓዊና ዘላቂ መፍትሔ መስጠት የሚገባ መሆኑ ታውቆ የሰውን ሕይወት ከማጥፋትና ሕብረተሰቡን አላስፈላጊ ሽብርና ሁከት ውስጥ ከማስገባት ተቆጥቦ ሕዝቡ ለጠየቀው ሕጋዊ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ በአጽንዖት እንጠይቃለን።

5. የወላይታ ሕዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት ደሙን ያፈሰሰና አጥንቱን የከሰከሰ ሕዝብ መሆኑና ዛሬም በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር መሆኑ ታውቆ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያናጋ በማስመሰል በሕዝቡ ላይ ጥላሸት የሚቀቡ ሁሉ ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ በዚሁ አጋጣሚ እናሳስባለን።

6. በወላይታ ውስጥ አሁን የተከሰተውን ሁኔታ በመጠቀም እውነታውን በማዛባት በተለያዩ ሚዲያዎች አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በሕዝቡ ላይ እያደረሱ የሚገኙትን ሥነ ልቦናዊ ጥቃት እንዲያቆሙ እንጠይቃለን።

7. ሌሎች በተመሳሳይ ሁኔታ የሚገኙ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል የሚኖሩ ሕዝቦችም ሆነ መላው ሠላም ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ፣ የተለያዩ የሚዲያ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች በወላይታ ሕዝብ ላይ በገዛ አገሩ በመንግሥት እየደረሰበት ያለውን ጥቃት በደልና ግፍ አብረውን እንዲያወግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

8. በመጨረሻም በመላው ዓለም የሚገኙ ጠቅላላ የዲያስፖራ አባላት በወላይታ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል በጋራ እንድትቆሙ ይህ ታላቅ ግፍና መከራ እየደረሰበት ላለው ወገናችሁ የምትችሉትን ድጋፍ ሁሉ እንድታደርጉና ድምጻችሁን እንድታሰሙ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሠላምን ይስጥ!! #Wolaita #Ethiopia #Ethiopian Government Must Stop Attacking Innocent people of Wolayta!

ለCOVID-19 ድጋፍ በAWANA በኩል የተሰበሰበውን ገንዘብ በተመለከተ አጭር መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA) በትውልድ አካባቢያችን ብሎም በአገራችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የጤናና የኢኮኖሚ መቃወስ ውስጥ ሊገቡ ለሚችሉ ወገኖቻችን ድጋፍ እንዲሆን የገንዘብ መዋጮ ስንሰብስብ መቆየታችን ይታወሳል።

የተሰበሰበውን ገንዘብ ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች ወደ ወላይታ ለማስተላለፍ ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን እያለ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአገራችን በተነሳው የጸጥታ ችግር እና የኮሚዩኒኬሽን መቋረጥ በተለይ የስምምነት ዶኩሜንቶችን መለዋወጥ የማያስችል ሆኖ ገንዘቡን በመላክ ለተረጂው ወገን የማዋል ሒደቱ ተስተጓጉሎ ቆይቶአል።

በአሁኑ ሰዓት ግን ነገሮች በተሻለ ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው ከተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መገናኘት በመቻሉ የአዋና አመራር በጁላይ 26, 2020 ባደረገው ስብሰባ በፕሮጀክት ንድፈ ሀሳብ ላይ ተነጋግሮ ወደ ውሳኔ ሀሳብ ደርሷል። ይህ የውሳኔ ሀሳብ ሥራ ላይ ከመዋሉና ሕጋዊ የስምምነት ሰነድ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ከመፈራረማችን በፊት የገንዘብ ድጋፍ ካደረጉ ወገኖቻችን አስተያየት/feedback እንዲሰጠን ዝርዝር ማስታወሻ GoFundMe በኩል የተላከላችሁ በመሆኑ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ ይህን ተከትላችሁ አስተያየታችሁን እንድትሰጡን በአክብሮት እናሳስባለን።

እግዚአብሔር አገራችንንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

AWANA

በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በማስመልከት የተሰጠውን መግለጫ በመስማታችን የተሰማንን ታላቅ ደስታ እየገለጽን የአገራችን መንግሥት በአፈጻጸሙ ላይ ስለወሰደው ቁርጠኛ እርምጃ ያለንን አድናቆት በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን።(July 22, 2020)

በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በማስመልከት የተሰጠውን መግለጫ በመስማታችን የተሰማንን ታላቅ ደስታ እየገለጽን የአገራችን መንግሥት በአፈጻጸሙ ላይ ስለወሰደው ቁርጠኛ እርምጃ ያለንን አድናቆት በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን።

መላው የአገራችን ሕዝብ ለዚህ ታላቅና ፈር ቀዳጅ ልማታዊ ሥራ ስላሳየው አንድነትና ትጋት ምሥጋናችን የላቀ ነው።

አገራችንንና ሕዝባችንን እግዚአብሔር ይባርክ!!

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA)

Wolaitatto Lemiso Hasayata: Wolaita Asay dumma dummabata qantan birshshanaw go’ettiyo lo’iyanne keehippe mal’iya lemiso hasayatuppe amaradageeta garssan wottida. Wolaitay hayseyyiddi leemisoy yohuwa duttana xayikkone silisses yaages!

 Axare Wurssi Yootin Ashshi Qanxxes
 Aybi xayo kettan santti lochchan ka’i
 Aye Uloy Gazza Yeles
 Ayesi baynna sagayoy na’essi kushiya menttes
 Banan Be’ay Piton Koyes
 Battiya Baynasan Quuliyakka Bana Batta Gaws
 Bitta Baaqin Biray Kiyees
 Baqidage dogikonne baqetage dogenna
 Coray Cuchchidi Batta Kunttes
 Dafara Diyaaba Miida Kuttiyaa Daaguwaa Ootiya Garawa Bolli Kiyawsu
 Darin Guurin Darkkon Wonttes
 Daro Mana Gay Daboppe Attes
 Deshshiya Ba Liiqo Inxarssan Ooha Maws
 Gaanay De’ishin Gayttay Micces
 Giyay be’ana parssuwa gillan kamettes
 Gutta Duretay Yoota Yoota Gees
 Halittay ongichin hanira adharkina gin ay maddi?
 Hana Mata Koshsha Gidukku Leehe Koshsha
 Hariya Sangisanaw Para Gondorsettes
 Hargiyaa qottay xaliyappe attes
 Hariyara Pe’ida Mizziya Haretta Suqaws
 Hasayanappe Kasetada Qoppa
 Hattay Micishin Mees
 Hayqida Hare Godariyaw Yayenna
 Hayqiya Hariyan Awtiya Ekoppa
 Hentta Ixana Na’ay Lanquwaa Ixxes
 Goda hoota madenage ketta assa kexxa ges
 Deshiya kaciya mentta mentada bana uzze gaws
 Ishara de’iyara injjiyan duraws
 Henttay bennasa koshshay bees
 Hilla Daroy Xaphuwaa Qanxxes
 Issi Mize Goday Eretta Mike Ges
 Kaalin Pilay Cammes
 Kalisana Kattay Keriyan Erettes
 Kaloy Michche Xantta Oyttes
 Kana Boora Waaxin Shenderakko Goyes
 Kanay So Kare Mehenne Gidenna
 Kaareera kafafu ayyo sooni buleera gooseera manqqo.
 Karido Kattay Kawo Ayses
 Kaysoy Hamusa Wuqin Kanay Arba Bocces
 Kuha Qanxxay Aaci Erenna

 Lafa Madday Yimppo Ekes
 Lafa Na’ay Laata Nages
 Lafana hattay kana mees
 Lafa imattay iraw gelidi kahuwaa gishes
 Leemisoy Yohuwa duttana Xayikonne Silisees
 Mana goromotiyaa loome gaws
 Iimatta boora mizziya qaycaws
 Mangaagi mal’o be’in shakilay baqa ekkes
 May Mal’o Eres Mayay Ho’o Eres
 May Malapenne Wolqappe Xayi Erenna
 Miiiday Biida Gakkes
 Modhana Goy Mogana Gates
 Muqoy Bana Gakenna Qefiya Zalla Mayzes
 Oolinne Na’inne Woxxa Genna
 Ootiday Mana Azallay Lawishin
 Qaacuwaadan Cincca
 Qanate Qammoppo
 Qeri Eray Yoota Yoota Ges
 Qeri Naatura Tushkiyo Barbare Qesiya Oyqes
 Qoppi Aqin Bukki Aqees
 Saruwan Santtay Keeha
 Shoshay so gelid dawe kiyes
 Siyenna hayttay shorora moores
 Soy Goyyes Gin Kare Woygane?
 Sunitti baynna kanay tita gishin hayqqes
 Tuma Yootin Xossay Doses
 Ubba Baynara Cum’u Gin Mana Gaws
 Udunxxa Uutidinne Dexenna Dendidinne Kawyenna
 Ulo Mishshoy Quma Katenna
 Utetta Daroy Zeretta Conches
 Waani Xaagane Giido Booray Himbaa Ges
 Waase Menna Mishsha Qanxes
 Wode dishin woxxa, Aaway de’ishin Xee’a
 Iitay iyissi cayees
 Geleshoy geman ta aawa mizzay xeetaa gees
 Wolqi ixxoy Xossan Cayes
 Wora Simada Gerera

 Woreray Woxin Qonashe Qaxxes
 Wozani Worin Azini Yeddes
 Xesenan Yiiday Koyenan Bees
 Xesenan yiida imattay kahuwaa gishes
 Yeesaamiya Cooray Mara Wores
 Zayroy Ba Karen Minnes
 Zokkoy Ixxin Ottay Uloy Ixxin Commes
 Zorin ixxay zoodi be’es
 Akekenna Geressay Zaarishin Metes
 Amanetto Mashshay Tiriyan Meqqes
 Ashshuwaa Qooda Gin Lanxxiya Qooday?
 Away Dishin Woxxa,Aaway De’ishin Xe’a

በወላይታና አከባቢዉ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ (June 25, 2020)

በወላይታና አከባቢዉ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ
በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ
June 25, 2020
የወላይታና አጠቃላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ መዋቅራዊና ስልታዊ (systemic) በሆነ መንገድ በሚፈጸምበት መንግሥታዊ ጭቆናና
አፈና ለዘመናት ጎብጦ የኖረ ሕዝብ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ከዚሁ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ በደል ለመላቀቅ ላለፉት በርካታ
ዓመታት የፍትሕና የመሠረታዊ መብት ጥያቄ በማቅረብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲታገል መቆየቱም ይታወሳል። ከሕዝቡ የትግል
አቅጣጫዎች አንዱ ክልል በመሆን ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገ-መንግሥታዊ መብት ማግኘት በመሆኑ ከቀበሌ አደረጃጀት አንስቶ እስከ ዞን
አስተዳደራዊ መዋቅር ድረስ ሕዝቡ ተወያይቶ በአንድ ድምጽ ለሚመለከተው የመንግሥት መዋቅሮች ሁሉ በማስታወቅ ፍትሓዊና ሕጋዊ መፍትሔ
ሲጠባበቅ ቆይቶአል። በተለይም አንጻራዊ የለውጥ ብርሃን በፈነጠቀበት በዚህ ጊዜ ጉዳዩ በመንግሥት በትኩረት ታይቶ ወቅታዊና ተገቢው ምላሽ
ይሰጣል ተብሎ መጠበቁ ተገቢ ነበር።
ሕዝቡ ያቀረበውን ሕገ-መንግሥታዊና መሠረታዊ የመብት ጥያቄ በአግባቡ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በኮማንድ ፖስት በማፈን፣ በኮሚቴ
እየታየላችሁ ነው፣ ሳይንሳዊ ጥናት እየተደረገበት ነው በማለት፣ እንዲሁም በሠላም አምባሳደሮች ይጠናል በሚሉ የጊዜ መግዣ በሚመስሉ
ማንከባለያዎች በመጠቀም የሕዝቡ የመብት ጥያቄ ተገቢ መልስ ሳይሰጠው ሲጓተት ቆይቶአል። በአሁኑ ጊዜ ይኼው ሁኔታ ግለቱንና ጡዘቱን
ጨምሮ የወላይታን ሕዝብ እርስ በራሱ ወደማተራመስና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ወደማጋጨት ደረጃ እየደረሰ መሆኑ ይስተዋላል። በመሆኑም
ይህ ሁኔታ በእጅጉ ያሳሰበው በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር ከመላው ዓለም የአካባቢውን ተወላጆች ሐሳባቸውንና
ስሜታቸውን እንዲገልጡ ባለፉት ሳምንታት መድረኮችን በማዘጋጀት በስፋት ውይይት ተደርጎበታል። በነዚህ የውይይት መድረኮች ላይ
የተንጸባረቁ ሓሳቦችን መነሻ በማድረግ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የአቋም መግለጫዎች አውጥቶናል።

  1. የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የወላይታ ሕዝብ በአገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የራሱን ድርሻ በሚገባ ማበርከት እንዲችል፣ የኢኮኖሚ
    ልማትም ፍትሓዊ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል፣ ባሕልና ቋንቋውን ማሳደግ እንዲችል፣ ባልተንዛዛ ቢሮክራሲያዊ አስተዳደር አገልግሎት
    ማግኘት እንዲችል እና በአገሪቱ መንግሥትና ሕግ እኩል መታየት እንዲችል ሕገ መንግሥቱ ያጎናጸፈውን ዕድል በመጠቀም ራሱን በራሱ
    ለማስተዳደር ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይና ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።
  2. የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የወላይታን ሕዝብ ሠላማዊና ሕጋዊ ጥያቄ ትርጉሙን ለማዛባት በለውጡ ማግስት እያመጹ ከሚገኙ ከተለያዩ
    አካላት ጋር በማያያዝ የወላይታን ሕዝብ ስም የማጉደፍ፣ የጥያቄውን ተገቢነት ለማደብዘዝ፣ ብሎም የህዝብን ትዕግስት እንዲሟጠጥና
    የአካባቢውን ሰላም በማናጋት ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት ተብሎ የሚሰራው አደገኛ ሸፍጥና ሴራ በአስቸካይ
    እንዲታረምና ህጋዊ የሆነው በክልል የመደራጀት ጥያቄ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሠረት እንዲመለስ እንጠይቃለን::
  3. የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የወላይታ ሀዝብ ጥያቄ በማያሻማ ቃላት የተገለጸ ራስን በራስ ማስተዳደር እንጂ የማዕከልና የክላስተር ጥያቄ አለመሆኑን
    ሕዝቡና ተወካዮቹ በተደጋጋሚ ገልጸዋል እየገለጹም ነው። ይህ እውነታ በግልፅ እየታወቀ በተቀናጀ መንገድ ከአጎራባች ወንድም ህዘቦች ጋር አላሰፈላጊ የሆነ
    ግጭት ለመፍጠር በህዝባችን ላይ እየተካሄደ ያለው የተደራጀ ሴራና ስም የማጥፋት ዘመቻና ዕኩይ ድርጊት ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ከግምት ውስጥ
    በማስገባት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በአፋጣኝ እንዲያስቆም እናሳስባለን።
  4. መላው የወላይታ ሕዝብ በበኩሉ ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊና ህገ-መንግሰታዊው ራስን በራስ የማሰተዳድር ጥያቄ የህልውናው ጥያቄ በመሆኑ በአንድነት መንፈስ
    እስከፍጻሜው በሠላማዊ ና ሕጋዊ መንገድ ብቻ በፅናት እንድትታገሉ በአክብሮት እንጠይቃለን:: በዚህ ሰላማዊ ትግል እንደ ሲቪክ የዲያስፖራ ማኅበር
    ከጎናችሁ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እናረጋግጣለን፡፡
  5. በተለያየ የዓለም ሃገራት የምትኖሩ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች በወላየታ ህዝብ ላይ እና በአጠቃላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን
    የአስተዳደር በደልና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በምትኖሩባቸው ሃገራት ላሉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ለተለያዩ ተቋማትና ሕዝቦች፣ ዓለም አቀፍ
    የሰብዐዊ መብት ድርጀቶችና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በማሳወቅ በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ትክክለኛ አቅጣጫ እንዲይዝ ጫና ለማሳደር
    የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እያሳሰብን ያስተማራችሁን ማህበረሰብና የጋራ ሀገራችን ኢትዮጵያንም የምትረዱበት ወሳኝ ወቅት ላይ በመሆናችሁ በተለያዩ
    ሚዲያዎችም ጭምር የሕዝቡን ድምፅ እእንድታጎሉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
  6. የወላይታ ዞን ምክር ቤትና የሕዝቡ ተወካዮች ምንም እንኳን የዘገየ ቢሆንም የክልልሉን ምክር ቤት ባለመሳተፍ ካሳያችሁት ቁርጠኝነት ጀምሮ ባወጣችሁትም
    የአቋም መግለጫ ያለንን አድናቆት እየገለጽን አሁንም የሕዝብ አገልጋይነታችሁንና ወገንተኝነታችሁን በጽናት እስከመጨረሻው እንድትቀጥሉ እያሳሰብን
    የወላይታን ዲያስፖራ እያስተባበረ የሚገኘው ማኅበራችን ከጎናችሁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ያስታውቃል።
  7. በመጨረሻም የወላይታ የክልልነት ጥያቄ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ በዚሁ ጉዳይ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ ለማበርከት መስዋዕት በመክፈል ላይ ለምትገኙ
    በመንግሥት ኃላፊነት የምትገኙ የሕዝቡ ተወካዮች፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት መሪዎች፣ የላጋዎች፣ ስላሳያችሁት
    ትጋት ሁሉ ያለንን አድናቆት እየገለጽን ጉዳዩ እልባት አግኝቶ የሕዝቡ ጥያቄ በቂ ምላሽ እስኪያገኝ ለዚህ የሕዝብ አጀንዳ በጋራ ሕግን ባልጣሰና ሠላማዊ
    በሆነ መንገድ መታገላችሁን እንድትቀጥሉ እናበረታታለን።
    ኢትዮጵያንና ህዝቦቹዋን እግዚአብሔር ይባርክ።
    በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA)

በዝዋይና በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች በሚኖሩ የወላይታ ተወላጆች ላይ እየደረሱ ያለዉን ጥቃት በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ። December 10, 2017

ወላይታ |”ዋላሄታ”| የወላይታ ብሄር መጠሪያ ስምና የመኖሪያ ቦታ ሲሆን ትርጓሜውም የተቀላቀለ፣ የተደባለቀ፣
የተዋሀደ፣ የተቀየጠ ማለት ነው። አሁን ወላይታ በሚባልበት አካባቢ የሚኖረው ህዝብ ከብዙ ዘመናት በፊት ከሀገሪቱ
ከተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ ነገዶች መጥተው በአካባቢው ከሚኖሩት ነገዶች ጋር በመዋሃድ የተመሰረተ ብሄር ነው።
በተለያየ ምክንያት ማለትም በንግድና በሌሎች ስራ ምክንያት በመምጣት ከነዋሪው ህብረተሰብ ጋር በመላመድና
በመዋሃድ ወደመጡበት ቀዬ ሳይመለሱ የቀሩና እስካሁን ድረስ የመጡበትን ብሄር ወይም ኣከባቢ ስም ይዞ ግን ወላይታ
በመሆን የሚኖር በርካታ ጎሳዎች (Clans) በወላይታ ውስጥ ይገኛሉ። ከነዚህም ውስጥ ከሰሜን ትግሬና አማራ፣
ከኦሮሚያ፣ ከከፋ፣ ከጉራጌ ፣ ከሲዳማ ፣ ከጌዲኦ እና ከአማሮ ኬሎ እንዲሁም አጎራባች ከሆኑት ከጋሞ፣ ከቦሮዳ፣ ከቁጫ፣
ካዳውሮ፣ ከከንባታና ሃዲያ አካባቢ የመጡ ይገኙበታል። ይህ ጥንታዊ የሆነ የወላይታ ብሄር እስከ 19ኛው ክፍለዘመን
መባቻ ድረስ የራሱ የሆነ መንግስታዊ ስርአት የነበረዉ ሲሆን ንጉሳዊ አስተዳደርም በአካባቢው ከነበሩት መንግስታት
እጅግ ገናና ከሚባሉ አንዱ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይገልጻሉ።
ይሁን እንጂ ይህ የወላይታ ንጉሳዊ ስርአት መንግስት በ19ኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያን በአንድ ማእከላዊ
መንግስት ለማስተዳደር አቅዶ በተነሳው በያኔው የሸዋ ንጉስ ሚኒሊክ ጦርነት ተካሂዶበት ነበር። ይህ እልህ አስጨራሽና ደም
አፍሳሽ የሆነው ውጊያ በሁለቱ መንግስታት መካከል ለረዥም ጊዜ በበርካታ ዘሮች የተካሄዱ ሲሆን፤ በመጨረሻም በጦር
አውደ ውጊያ ሳይሆን ከውስጥ በወጡ ባንዳዎች አማካኝነት መረጃ ተሰጥቶ ጦርነቱ ሊጠናቀቅ ችሏል። በእንዲህ አይነት
ሁኔታ የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግስት አካል የሆነው ወላይታ እየዋለ እያደረ የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት አምኖ
በመቀበል ለአንድ ሉአላዊ ሃገር ግንባታ ከሌሎች ብሀረስቦች ጋር በመሆን አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ አበርክቱዋል፤
እያበረከተም ይገኛል። ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ደሙን አፍስሶአል፤ አጥንቱን ከስክሷል፤ ህይወቱን ሰውቷል፤ ውድ
ልጆቹን ለዳር ድንበር መከበር ገብሯል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንዲሁም አብሮነትና ወንድማማችነት ከምንም በላይ
ትልቅ ዋጋ ያላቸው ነገሮች መሆናቸውን ጠንቅቆ ይገነዘባል። በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ ብሄራሰቦች በኢትዮጵያ
መጻኢ እድል ውስጥ እኩል ድርሻ ያለቸው መሆኑን ያለማወላወል ያምናል። ማንኛውም ብሄረሰብ በማንኛውም ሁኔታ
ከሌላው የማይበልጥ ወይም የማያንስ መሆኑን በጥልቀት ይረዳል፤ ሁሉም ብሄረሰብ እኩል መሆኑን በአጽኖት ያምናል።
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ወላይታ እንደቀደሙት አያቶቻችን ጊዜ እንደሆነው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች በግልና
በመንግስት ስራ፣ በንግድና ሃብትን በማፍራት፤ በጋብቻና እንዲሁም በሰፈራ በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያዊ የሆኑ ወገኖች
በግለሰብ፣ በቤተሰብ በድርጅትና በማህበረሰብ ደረጃ እየመጡ በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት እንደሚደረገው ሁሉ
በወላይታም ይኖሩበታል። የወላይታም ህብረተሰብ የሚመጣውን ኢትዮጵያዊ ወገኑን ዘር ወይም ቀለም ሳይለይ፤
ሀይማኖት፣ ጾታና የመጡበትን አካባቢ ሳይመርጥ/ሳይለይ ሁሉንም በእኩል አይን በማየት በፍቅር አስተናግዷል።
የወላይታ ህዝብ ሰው ወዳድነት እንግዳ ተቀባይነት እና ወንድማዊ ፍቅሩ ማርኩዋቸው ባህላችሁ ባህላችን ታሪካችሁ
ታሪካችን ብለው፣ ኑራቸውን ወላይታ ውስጥ ያደርጉ በርካቶች ናቸው። በተመሳሳይ ሁኔታ በርካታ የወላይታ ተወላጆችም
ከቀዬአቸው ርቀው በመሄድ በሃገሪቱ ተዘዋውረው በተለያዩ የኑሮ ደረጃ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የእለት ኑራቸውን
እየገፉ ይገኛሉ።
በዚህ አይነት ሁኔታ ከትውልድ ቀዬአቸው ተነስተው ከሄዱ የወላይታ ተወላጆች በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ አካባቢ
የሚኖሩ ይገኙበታል፤ እነዚህ ኢትዮጵያዊ የወላይታ ተወላጆች አንዳንዶቹ በአካባቢው ረዥም ጊዜን ያስቆጠሩ ሲሆኑ
ሌሎቹ እግሞ በቅርብ ጊዜ በስራ ምክንያት የሄዱ ናቸው። እነዚህ ወገኖች ሰላማዊ ኑራቸውን እየመሩ ከአካባቢው
ህብረተሰብ ጋር በሰላም ወጥተው በሰላም ገብተው በማንኛውም ሁኔታ የአካባቢው ህብረተሰብ ስጋት ሳይሆኑ የሰላምና
የፍቅር አጋር ሆነው በአብሮነትና ወንድማማችነት በኢትዮጵያዊ ባህል እየኖሩ የእለት ተእለት ስራቸውን የሚያከናውኑ
ናቸው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእነዚህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ብሄረሰብን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየደረሰባቸው
እንደሆነ የተለያዩ የመገናኛ አውታሮች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ከአካባቢው የሚመጡ የአይን ምስክሮችና የጥቃቱ ሰላባ
የሆኑት ወገኖች ከሚናገሩት ለማወቅ ተችሏል። ይህ ድርጊት እጅግ ዘግናኝ የሆነና አሳዛኝ ነው። በዚህም ልባችን በጣሙን
አዝኗል። ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉና ሰባዊ ፍጡር ሁሉ ያዘነበትም ነው፤ ሊወገዝም የሚገባው ነው።
እኛ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ኢትዮጵያዊ የሆንን የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ይህንን ክስተት ስንሰማ
በድንጋጤ ተውጠን ምን እየተደረገ ነው? ወዴት እየሄድን ነው? ብለን እራሳችንን እንድንጠይቅ አስገድዶናል። የወላይታ
ተወላጅ የሆነ ግለሰብ፤ እንድማንኛም ኢትዮጵያዊ ኦሮሚያ ዝዋይ አገሩ እንደሆነ እናምናለን፤ እንዲሁም ጎንደርም
ጎጃምም፣ ጂማ፣ ሀረርጌ፣ ሶማሌ ወዘተ አገሩ ነው። ነገር ግን የወላይታ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ምንም አይነት
ምክንያት ሊቀርብበት በማይችል ሁኔታ ለብዙ ዘመናት ከኖረበት አካባቢ እንዲፈናቀሉ ሲደረግ፤ ህጻናትና አቅመደካማ
አዛውንቶች ድብደባና እንግልት ሲደርስባቸው፣ ቤታቸውና ንብረታቸው ሲቃጠልና ሲወድም፤ ሰዎች በግፍ ሲገረፉና
ሲገደሉ መስማት በጣም ያማል። ከዚህም አልፎ ተርፎ የአስተዳደር በደል ደረሰብኝ፣ ፍትህ ተንፈግኩኝ፣ ሙስና
በመንሰራራቱ አገር መልማት አልቻለችም በማለት በህዝባዊ አመጽ ተቃውሞን እየገለጸ ያለው የኦሮሚያ ወጣት የህዝብ
ማመላለሻ መኪናዎችን የመንግስት የግል መኪናዎችን እያስቆመ ወደ ውስጥ በማስገባት “ወላይታ አለ?” እያለ ለግልና
ለመንግስት የስራ ጉዳይ እንዲሁም ለማህበራዊ ጉዳይ በዝዋይና ሻሸመኔ አካባቢ በማቋረጥ የሚመላለሱትን የወላይታ
ተወላጆችን እያወረዱ ድብደባ እንግልትና ስቃይ እየተፈጸመባቸው እንደሆን እየተነገረ ነዉ። በጣም የሚገርመው ደግሞ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለህዝቦች አንድነትና እኩልነት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቆርጬ ተነስቻለሁ እያለ
በሚሰብክበት ጊዜ ይህ ሁኔታ መፈጠሩ ነው። ኢትዮጵያዊነት ኦሮሞ ብቻ አይደለም፤ አትዮጵያዊነት አማራ ብቻ
አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት ወላይታም ጭምር ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ሁሉንም ብሄር የሚጨምር ነው። ሙሉና ግማሽ
ኢትዮጵያዊ የለም፤ ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን እንደሆነች እናምናለን።
ስለዚህም እኛ በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆንን የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ከሌሎችም በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆኑ
ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመወያየትና በመመካከር የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ ሁሉ
በአክብሮት እናቀርባለን።

  1. የወላይታ ተወላጆች እንደማንኛም ኢትዮጵያዊ ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው የመስራት፣ ሀብት የማፈራት እና
    በሰላም የመኖር ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው እንዲከበርላቸው ፤
  2. የኦሮሚያ መስተዳደር ወንጀለኞቹን ለፍትህ የማቅረብ ስራውን በፍጥነትና በሙሉ ፍትሃዊነት
    እንደሚያጠናቅቅ ተስፋ እያደረግን ውጤቱ ለተጎጂውም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ በመገናኛ ብዙሃን
    እንዲገለጽ ፤
  3. ለሞቱት የወላይታ ተወላጆች ቤተሰቦች አግባብ ያለው ካሳ እንዲከፈል፣ ቤትና ንብረት ለተቃጠለባቸው
    ለተዘረፈባቸው ተገቢ ካሳ እንዲከፈላቸው ፤
  4. የፌደራል መንግስት የኦሮሚያ መስተዳደር የደቡብ ብሄር መስተዳደርና የወላይታ ዞን አስተዳደር ይህን ጉዳይ
    በሃላፊነት የሚከታተል ቡድን ፈጥሮ ሂደቱንና ውጤቱን ለመላው የደቡብ ህዝብ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ፤
    እንዲሁም በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ይፋ እንዲያደረግ በአክብሮት እንጠይቃለን።
    እግዚኣብሔር ኢትዮጵያን ይባርካት!
    በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር።

በወላይታና በሲዳማ ህዝቦች መካከል የመሬት ይገባኛል ጉዳይ ከሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር የተሰጠ መግለጫ July 4, 2017

በአሁኑ የኢትዮጵያ የመልክአምድር አቀማመጥ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የወላይታ ብሄረሰብ ይህንን ቦታና ስያሜ ይዞ የተቀመጠው ከብዙ ሺህ ዘመናት በፊት እንደነበረ የታሪክ መዛግብት ያመለክታሉ። ይህ ጥንታዊ የሆነው ብሄረስብ በሁሉም አቅጣጫዎች መሰል ከሆኑ በርካታ ብሄረሰቦች ጋር የሚዋሰን ሲሆን፤ በሰሜን ከከምባታና ሃድያ፣ በሰሜን ምስራቅ ከኦሮሚያ፣ በምስራቅ ከሲዳማ፣ በደቡብ ከጋሞና ቁጫ እንዲሁም ደግሞ በምእራብ ከዳውሮ ጋር ይዋሰናል። ወላይታን ከነዚህ ሁሉ ብሄረሰቦች ጋር የሚያዋሰነው ወሰን የተወሰነዉ በታሪክና ብሄረሰቦቹ እርስ በርስ በመተማመን ያበጁት የጋራ ድንበር ነው እንጂ ማንኛውም የዉጭ አካል በመሀከላቸው ገብቶ ገመድ መትረው ችካል ቸክለው የወሰኑት አልነበረም። አሁን ወላይታ የሚገኝበት ወሰን፣ ድሮ በንጉሳዊ አገዛዝ በሚተዳደርበት ጊዜም ሆነ የወላይታ የንጉሳዊ ስርአት እና የራስ አስተዳደር እልህ አስጨራሽ በሆነው በምኒሊክ ጊዜ በተደርገው ጦርነት ተገርሰሶ ወላይታም የማዕከላዊ የኢትዮጵያ የመንግስት አካል ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ በማንኛውም መልክ ያልተሸራረፈ እና ያልተቀየረ ነበር። የወላይታም ብሔር እላይ ከጠቀስናቸው አጎራባችና ወንድም ከሆኑ ብሔረሰቦች ጋር እርስ በእርስ በመፈቃቀርና በመተሳሰብ የጋራ የሆኑ የታሪክ፣ የባህል፣ የማሕበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ እሴቶችን በመጠበቅ ፣ በማክበርና በመከባበር ለዘመናት አብረው ኖረዋል፤ አሁንም እየኖሩ ይገኛሉ። ይህ ሲባል ግን በማንኛውም ሁኔታ በወላይታና አጎራባች ከሆኑ ብሔረሰቦች ጋር ያለመግባባት ተፈጥሮ አያውቅም ማለት አይደለም። እንደማንኛውም በጋራ እንደሚኖር ማህበርሰብ እና የጋራ ድንበር ከሚኖራቸው ብሔረሰብ ጋር እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ ግጭት እንደሚፈጠር ሁሉ በወላይታና በእነዚህ በአጎራባች ብሔረሰቦች በተወሰነ መልኩ ከቀላል እሰከ መለስተኛ ግጭት በተለያዩ ጊዜያት ይፈጠር ነበር። ይሁን እንጂ እነዚህ ግጭቶች ወይም አለመግባባቶች ብሔረሰቦቹ ለዘመናት ባካበቱት የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ የመፍታት ልምድ ካለማንም ጣልቃ ገብነት ይፈቱት ነበር። ይህ ባህላዊ ስርአትና ተቋም ህብረትሰቡ በመፈቃቅድ እና በመቻቻል እንዲኖሩ ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክቷል። አሁንም ይህ የመፈቃቅድና የመቻቻል ባህል በተጠናከረ መልኩ ቀጥለው እነዚህን ብሔረሰቦች ይበልጥ እያቆራኛቸውና እያስተሳሰራቸው ይገኛል። ይህም በአካባቢያቸው ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን እንዲፈቱ በማገዝ የእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያቸው ጤናማ በሆነ መልኩ እንዲቀጥል እጅግ እረድቶአል።

ሆኖም እዚህ ጋ አጽንኦት ሊሰጥው የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ወላይታ ከሚያዋስናቸው አብዛኛውዎቹ ብሔረሰቦች ጋር በሚያገናኛቸው የድንበር አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁሉም በኩል ተመሳሳይ የሆነ የአኗኗር ዘዴ ያላቸው ማለትም አብዛኛዎቹ በእርሻ ስራ የሚተዳደሩ ናቸው።  ይሁን እንጂ ወላይታን በምስራቅ በኩል የሚያዋስነው ወንድም የሆነው የሲዳማ ህዝብ በተለይ በድንበር አካባቢ የሚኖረው ማህበረሰብ በአብዛኛው ከበዙ ዘመናት ጀምሮ በእንስሳት እርባታ የሚተዳደር አርብቶ አደር ነው። ይህ ወንድም የሆነው የሲዳም ህዝብ ለእንስሳቶቹ ሳርና ውሃ በሚያጥርበት በበጋ ወቅት የወላይታን ድንበር ተሻግሮ የወላይታ ቆላማና ለም መሬት ላይ እንስሳቶቹን በማሰማራት የወላይታን መሬት ይገለገል ነበር። የወላይታም ህዝብ እንግዳ በመቀበል ድንበር ተሻግሮ በግዛቱ እንስሳዎቹን እያሰማራ የሚገኘውን የሲዳማን ብሔረሰብ ካላንዳች ችግር የበጋ ወቅት እስኪያልፍ እንስሳቱን እንዲያሰማራ ይፈቅድ ነበር። የሲዳማ አርብቶ አደሮቹም የዝናብ ወቅት ሲመጣ ጓዛቸውን ጠቅልለው እንስሳቶቹን እየነዱ ወደመጡበት ወደ ሲዳማ ግዛት ተሻግረው ይመለሱ ነበር። ይህ ሁኔታ ለብዙ ጊዜ እየተደጋገመ በመምጣቱና እንግዳ ተቀባይ ከሆነው ከወላይታ ሕዝብ ጋራ እጅግ በመላመዳቸው አንዳንዶቹ ባህላችሁ ባህላችን፣ ወጋችሁ ወጋችን በማለት ጋብቻ በመመስረት ጎጆ ቀልሰው ኑሮአቸውን በወላይታ ግዛት ውስጥ እንዳደረጉ ይታወቃል። እንደዚህ ባለ ሁኔታ በወላይታ ግዛት ውስጥ መስፈር የጀመረው የሲዳማ ህዝብ ለረጅም ዓመታት በሚኖረበት ጊዜ አንዳችም የሆነ የግዛት ችግር ሳይኖርበት አስተናጋጅ የሆነው የወላይታ አስተዳደር በሚፈቅደው መሰረት አስፈላጊውን የነዋሪነት ግዴታውን እየፈጸመ ይኖራል።

ይሁን እንጂ፣ በቅርብ ጊዜ ከወደ ወላይታ አካባቢ የሚሰማው ወሬ እና እንዲሁም በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች የሚዘገበው ዜና ከላይ ከጠቀስናቸው እውነታዎች የሚቃረኑ ሆነው ተገኝተዋል። በቅድሚያ እንስሳቶቹን ቀጥሎ ደግሞ ቀስ በቀስ ኑሮውን በወላይታ ታሪካዊ ግዛት ውስጥ መስፈር የጀመረውና አሁንም እየኖረ ያለው ወንድም የሆነው የሲዳማ ብሔረሰብ የሰፈረበት ቦታ ለሲዳማ ተላልፎ እንዲሰጥ መወሰኑ እየተነገረ ነው። ይህ ቦታ የወላይታ ብሄረሰብ ታሪካዊ ይዞታ ሲሆን በእንግድነት የሰፈረው የሲዳማ ብሔረሰብም አብሮ ተስማምቶ ተፈቃቅደው እና ተቻችለው ከመኖር ውጪ በማንኛውም መንገድ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ አንስቶ አያውቅም። ሁለቱም ወገኖች ድንበራቸውን እና ወሰናቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁና ከዚህ በፊትም በድንበር አካባቢም ሆን በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ አለመግባባትን በጋራ የመፍታት የዳበረ ልምድ ያላቸው ናቸው።

በኣሁኑ ወቅት ያለዉ ሁኔታ የተፈጠረዉ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ በነዋሪዎች የጋራ መግባባት ሳይሆን በአስፈጻሚ አካላት ውሳኔ የወላይታ ታሪካዊ መሬት ለሲዳማ ተላልፎ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑና ይህም የበላይ ኣካል ዉሳኔ በህዝቡ ላይ በግድ ወደመጫን እያመራ እንደሆን በስጋት ይነገራል። ይህ ኣካሄድ ሁለቱ ተስማምተውና ተፈቃቅደው የቆዩትን ብሔረሰቦች ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ስጋት አለ። ይህ ጉዳይ በጥንቃቄ ካልተያዘ በአካባቢው የማያባራ ግጭትን ሊፈጠር እንደሚችልና አላስፈላጊ የሆነ መናቆር ብሎም ደም መፋሰስ ሊያስከትል እንደሚችል አያጠራጥርም። ከዚህ የተነሳ አሁን እያጣጣሙት ያለውን ሰላምና ወግ እንዲፈርስ በማድረግ በአካባቢው ውጥረት ሊያነግስ ስለሚችል እኛ በሰሜን አሜሪካ የምንኖር የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ይህንን በህዝቦች መካከል ግጭትን፣ ጥላቻንና አለመግባባትን ሊያስፋፋ የሚችል ኣካሄድን አስፈጻሚ አካላት ቆም ብሎ በማሰብ ሁኔታዉን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በፍትሃዊነትም ጭምር እልባት ማግኘት እንዲችል ይህን መሰል ሁኔታዎችን ፣በጋራ በመፍታት እጅግ የዳበረ ልምድ ያላቸውን የሁለቱን ብሔረሰብ አካላት እድል እንዲሰጣቸውና ከሁለቱም ብሔረሰቦች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች፤ ምሁራንና ሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተ አካል ተመስርቶ ለጉዳዩ እልባት እንዲሰጡ ስንል በአጽንዎት እንጠይቃለን።

አስተማማኝ ሰላምና ፍትሃዊንት ለሁሉም ህዝቦች እንመኛለን!

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር

News/Blogs

Awana Wolaita at a Glance: Success in Education and Community Development (2025)

Awana Wolayti Luxettaaninne Deretetta Dichchan 2018 ML Ottido Oosota xeelliyaagaan kaalidi de’iya YouTube be’anaw shoobettideta: https://youtu.be/Vv956eBgRVwበ2018 ዓ.ም. አዋና ወላይታ በትምህርትና በማህበረሰብ እድገት ያከናወነዉን ትልቅ ስኬት ለማየት ከታች ያለውን የYouTube ቪዲዮ ይመልከቱ።Watch the following YouTube video to see Awana Wolaita’s 2025 achievements in education and community development in Wolaita.

በ AWANA – Association of Wolaita’s and Allies in North America የተገነባው ት/ት ቤት ተመርቋል

“የመማር ማስተማር ሥራዎችን ለማሳለጥ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው” ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ዳሞት ወይዴ፤ መስከረም 25/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ዳጋጋ ሌንዳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት 6 አዳድስ ክፍሎች ግንባታና ያረጁ ክፍሎች ጥገና በ(AWANA) በአሜሪካ ያሉት ወላይታ ተወላጆች የተገነባው ት/ት ቤት ተመርቋል ። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ…

በወላይታ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የመብት ጥሰትና አፈናን በተመለከተ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA) እና በዋሽንግተ ዲሲ አካባቢ የወላይታ ኅብረት (WCDC) በጋራAugust 9, 2022 ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው የወላይታ ብሔር በኢትዮጵያ ታሪክና አገር ግንባታ ሂደት ከሌሎች የአገራችን ህዝቦች ጋር ኢትዮጵያን በማልማት፣ አንድነቷንና ሉአላዊነቷን በማስከበር ረገድ የሕይወት መሥዋዕትነት ሁሉ እየከፈለ የኖረ ኩሩና አገር ወዳድ ሕዝብ መሆኑን ማንም አይክደውም። አገራችንን ከፀረ-ሠላም ኃይሎች ለመታደግ እንዲሁም…

Wolaytatto Odota

Wolayta dere kawotettan,………………..