AWANA

AWANA Eeso Yaa’aa/የ AWANA ጉባዔ/ AWANA Meeting

Saroy Ubbassi gido. Ubba AWANA yametinne Wolayta allalliyan qofa shakkanaw koshshay de’iyo oonne, 02/27/2021 DC wodiya qoodan 8:00 PM ZOOM’ iya galchchan bettana mala, AWANA Osuwa polissiya kaletay shobbes. Ha ya’an dumma dumma qofati machcha demmanaw dandayosona. Hayanninta ha ya’an bettidi entte qofa aahuwan wottana mana AWANAy shobbes.

ለመላው የAWANA ቤተሰቦች:-ነገ ቅዳሜ Feb 27, 2021 መደበኛ ስብሰባችን በ8:00PM (በዲሲ ሰዓት) በZOOM ይካሄዳል። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር በሚደረግበት በዚሁ ስብሰባ ሁላችሁም እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት ጥሪ እናደርጋለን። የዙም ሊንኩንም ከዚህ በታች አስቀምጠንላችኋል።

This is a gentle reminder of tomorrow’s (02/27) meeting. Time: Feb 27, 2021 02:00 PM Pacific Time; (5:00 pm eastern) Agenda items include follow ups and updates on current affairs, AWANA bylaws, what we can do next, any other ideas are welcome.

Join Zoom Meetinghttps://csus.zoom.us/j/6104645663Meeting ID: 610 464 5663

የAWANA ሥራ አስፈጻሚ

COVID-19 GoFundMe ን በተመለከተ ከአዋና የተሰጠ መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA) በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን ከፍተኛ ተግዳሮት የሆነው COVID-19 በወላይታ አካባቢ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ድጋፍ ከመላው አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን በGoFundMe አማካይነት ስንሰበስብ መቆየታችን ይታወሳል።

በተለያዩ ጊዜያት በመላው አገራችን ሲከሰት በነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ ምክንያት በተለይም ደግሞ በነሐሴ ወር በወላይታ በፌደራል መንግሥት ወታደራዊ ኃይል በንጹኃን ላይ የተወሰደው ጥቃት ካስከተለው አለመረጋጋት የተነሳ ፈንዱን ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ ለማውረድ ምቹ ሁኔታዎችን ማግኘት ባለመቻላችን ለተወሰነ ጊዜ መዘግየት እንደገጠመን ካሁን በፊት መግለጻችንም አይዘነጋም።

በአሁኑ ሰዓት ከዞኑ አስተዳደር ተወካዮች፣ ከጤና መምሪያ ተወካዮች እንዲሁም ሥራውን በበላይነት እንዲከታተሉ ከአዋና በኩል ከተመረጡት ተወካዮቻችን ጋር በመሆን በጥምረት የተቋቋመው ኮሚቴ አስቀድሞ በተቀረጸው ፕሮጀክት ፕላን መሠረት ተግባራዊ ለማድረግ የስምምነት ውል በመፈራረም ወደ ሥራው ተገብቶአል።

በዚሁ መሠረት ሥራውን እንዲያሳልጡና አፈጻጸሙን በበላይነት እንዲመሩ አቶ አሳምነት አይዛ፣ አቶ ላቀው ዋልቶሬ፣ አቶ ተስፋዬ ፈለሃ፣ አቶ አንዱዓለም ሰይድና ወ/ት እንጉዳይ መስቀለ በጥምረት ኮሚቴነት ተሰይመው ገንዘቡ ከGoFundMe ወጪ ተደርጎ ሊላክ ችሏል።

በፕሮጀክት ፕላን እንደተገለጸውና በስምምነት ውሉም ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ሥራው ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተወከሉ አካላት አማካይነት በውጤታማነት ሊሠራ የተጀመረ መሆኑን ለውድ አባሎቻችንና ወዳጆቻችን እየገለጽን የስምምነቱን ውልና የፕሮጀክቱን ፕላን ኮፒ እንዲሁም ገንዘቡን የላክንበትን ደረሰኝ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን መላካችንን እናስታውቃለን።

የሥራውን ሂደት እስከፍጻሜው እየተከታተልን በየጊዜው የምናስታውቃችሁ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንጠቁማለን።

እግዚአብሔር ሃገራችንንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

በዎላይታ ዲያስፖራ ማህበራት (AWANA, WIDA and WCWDC) ትብብር የሚካሄድ የድጋፍ ማሰባሰብያ

ይህ በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ እሁድ ታህሣሥ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጧቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት በደረሰው መነሻው ባልታወቀውና በዓይነቱ ከፍተኛ የሆነው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሀብት ንብረታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በውጭ ሃገራት  ነዋሪ ከሆኑ የአካባቢው ተወላጆችና ወዳጆች የድጋፍ ማሰባሰብያ ሲሆን በዚህ አዉዳሚ አደጋ የተጎዱ ዎገኖቻችንን ለማቋቋም ሁላችሁም ለወገን ደራሽና አለኝታነታችሁን በማሳየት ድጋፍ እንድታደርጉ በታላቅ አክብሮትና ፍቅር እንጠይቃለን።

የሚሰበሰበዉም ገንዘብ ለዚሁ አላማ በዞኑ አስተዳደር ወደተከፈተዉ የባንክ አካንት ገቢ የሚደረግ መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን።

https://charity.gofundme.com/o/en/campaign/fund-raising-on-the-fire-disaster-victims-in-wolayta-sodo

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (Awana Wolayta) አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ:-

ባለፈው ቅዳሜ December 5, 2020 የማኅበራችን ጠቅላላ ስብሰባ መደረጉ ይታወሳል። የጠቅላላ ጉባዔው ያለፈውን ዓመት ክንውኖችን በመገምገምና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ነበር የተጠናቀቀው።
በስብሰባው ላይ በመገኘት ከፍተኛ ተሳትፎ ላሳያችሁ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ሁሉ ያለንን አድናቆት በዚሁ አጋጣሚ እየገለጽን ለትውልድ አካባቢያችን ልማት፣ ማኅበራዊ ለውጥና ዕድገት የበኩላችሁን ድርሻ ለመወጣት በቀጣይነት ለምታሳዩት ፈቃደኝነትና መሰጠት ምሥጋናችን የላቀ ነው።
በስብሰባው ከተከናወኑት ተግባራት አንዱ የማኅበሩን ሥራ አስፈጻሚ አባላትንና የተለያዩ ዘርፍ መሪዎችን መምረጥ ነበር። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች ስማቸውና የሥራ ድርሻቸው በዝርዝር የተጠቀሰ ወንድሞችና እህቶች በጉባዔው የተመረጡ መሆኑንና እስከ ቀጣይ የምርጫ ዘመን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራ የተሰጣቸው መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
በመሆኑም:- ተመራጮች ሁላችንም በዚሁ ታሪካዊ ወቅት የተጣለብንን ሕዝባዊ አደራና ኃላፊነት ቸል ሳንል በታማኝነትና በቁርጠኝነት በመወጣት ለሕዝባችን ባለውለታነታችንን በተግባር እንድንገልጽ ይሁን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (Awana Wolayta) አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ:-

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (Awana Wolayta) አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ:-ማኅበራችን እፊታችን ቅዳሜ December 05, 2020 መደበኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ስብሰባ ያደርጋል። መሠረታዊና ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ በሚካሄደው በዚሁ ታሪካዊ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ሁላችሁም እንድትገኙ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።

ከአጀንዳዎቻችን ዋና ዋናዎቹ:-

1. አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታዎችን መገምገምና መመካከር፤

2. የAWANA COVID-19 Fund የሚገኝበትን ሁኔታ ማሳወቅ፤

3. የአመራር ምርጫ ማካሄድ፤

4. ሌሎች ከጉባዔው የሚነሱ ጉዳዮች ካሉ መወያየት፤ መሆናቸውን እያስታወቅን የመሰብሰቢያ ሰዓታችን 5:00PM Eastern time, 4:00PM Central time, and 2:00PM Pacific time መሆኑን እንገልጻለን። zoom link ቅዳሜ ጠዋት የምናሳውቃችሁ ይሆናል። AWANA Wolaita

አጭር ማሳሰቢያ

አጭር ማሳሰቢያ – በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር አባላት በሙሉ:-ባለፈው ቅዳሜ November 21, 2020 በነበረን የቦርድና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ስብሰባ ላይ በአንዳንድ ወቅታዊና አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መነጋገራችን ይታወሳል። በስብሰባው ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች ጥቂቶቹን ለማስታወስ ያህል:-1. ለኮቪድ-19 መከላከያ ድጋፍ በእኛ በኩል የተሰበሰበውን ገንዘብ ሥራ ላይ ለማውል እየተወሰደ ባለው እርምጃ ላይ በተለይም ከወላይታ ዞን ጤና መምሪያና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ጋር እያደረግን ስላለነው እንቅስቃሴ ተነጋግረናል።2. የተሰበሰበው ገንዘብ በምንም መልኩ ለተለያዩ ሥራ ማስኸጃዎችና አስተዳደራዊ ወጪዎች መዋል እንደሌለበት በመስማማት ድጋፉን ለተረጂዎች በማድረስ ረገድ ሊኖሩ ለሚችሉት አንዳንድ አነስተኛ ወጪዎች የሚሆን መዋጮ ማሰባሰብ እንዳለብን ተማምነናል።በመሆኑም በስብሰባው ላይ የተገኛሁትም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች መምጣት ያልቻላችሁ ወንድሞችና እህቶች የአባልነት መዋጮውን የስድስት ወር ወይም የአንድ ዓመት ገቢ እንድታደርጉና ከዚያም ጋር በማያያዝ ተጨማሪ ድጋፍ $5 $10 $20 $50 ወዘተ በአንድ ጊዜ ብቻ ድጋፍ በካሽ አፕ፣ በቬንሞ፣ በዘሌ እና በሌሎችም መንገዶች በመጠቀም ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።መዋጮአችሁን ለአዋና አካውንት ቀጥታ ለማስተላለፍ AWANA Account at Wells Fargo Bank Account # 3022905297 or ቼክ መላክ የምትፈልጉ በዌብ ሳይታችን በሚገኘው contact us” አዋና አድራሻ መላክ የምትችሉ መሆናችሁንም እናስታውቃለን።

Nomination for AWANA Leadership Positions 2020

Nomination for AWANA Leadership Positions 2020

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር በወላይታ ህዝብ ላይ በክልል መዋቅር ጥያቄ ምክያት እየደረሰ ስላለው ሕገ-መንግሥታዊና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ October 17, 2020

እንደሚታወቀው በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክና አገር ግንባታ ሂደት የወላይታ ብሄር ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመሆን አገሩን በማልማትና በመገንባትና ሉአላዊነቷን በማስከበር ጉልበቱን፣ እውቀቱን፣ ገንዘቡንና ውድ ህይወቱን የከፈለ፤ እየከፈለም የሚገኝ፤ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር፤ ጠንካራ፤ ሥራ ወዳድ እንድሁም ሰውን በዘሩ ሳይሆን በሰውነቱ (በሰብአዊነቱ) የሚወድ ኩሩ ህዝብ ነው ፡፡

ይሁን እንጅ በአጼዎቹ፣ በደርግና በኢህአደግ ዘመነ መንግስታት የየዘመኑ ገዥዎች ሆን ብለው አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ጫና በማድረግ የወላይታ ህዝብ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ መልማት በሚገባው ልክ እንዳይለማ፤ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ተቋዳሽ እንዳይሆን በረቀቀ መንገድ ሲጨቁኑ ኖረዋል፡፡ ሕዝቡ ከዚህ ጭቆና ለመላቀቅ ለረጅም ዘመናት ሲታገል የቆየ ሲሆን በተለየም ላለፉት ሁለትና ሶስት አመታት መላው የወላይታ ህዝብ ፍጹም ሰላማዊ፣ ህገ መንግስታዊና ዴሞክራሲዊ በሆነ መንገድ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱን በጨዋነትና በሰለጠነ መንገድ ሲጠይቅ እንደነበረ እውነተኛ ህሊና ያላቸው የሃገራችን መሪዎችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የሚያውቁት ሐቅ ነው።

ነገር ግን የፈደራልና የፈራሹ ደቡብ ክልል መሪዎች የዚህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ክብርና የሞራል ከፍታ በማይመጥን፣ ለሃገሩ ግንባታና ለዳር ድንበሩ መከበር የከፈለውን ዋጋ ባለመገንዘብ፣ ፍጹም ሃሰት በሆነ የፈጠራ ትርክት የህዝቡን ህጋዊና ግልጽ ጥያቄ እንደመመለስ “የወላይታ ህዝብ ከጸረ ሰላም ሐይሎች ጋር ግንኙነት አለው” በማለት በርካታ ንጹሐን እንዲሞቱ፣ እንዲቆስሉና የትግሉ መሪ የዞኑ አመራሮች በግፍ እንዲታሰሩ አድርገዋል። በተጨማሪም ለህዝቡ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ በመስጠትና በመረጧቸው መሪዎች እንዲመሩ በማድረግ ውጥረቱን ማርገብ ሲቻልነገር ግን መንግስት በከፋፍለህ ግዛ መንገድ የህዝቡን ሰላማዊ የመብት ትግል በታጠቁ የፈደራልና ክልል ጦር ኃይል በማፈን፣ ወጣቶችን በማሰርና በማሳደድ፣ ህዝቡ እርስበራሱ እንዲጠራጠር፣እንድሁም አከባቢው ተረጋግቶ ህብረተሰቡ በልማት ስራ ላይ እንዳያተኩር እያደረገ ይገኛል።

እንደዚሁም አስፈላጊ መስፈርቶች ሁሉ ተማልተው በዞን ም/ቤት ጸድቆ በክልል ም/ቤት አለአግባብ በመታፈኑ ፟ይግባኝ የቀረበለት ፈዴረሽን ም/ቤትም በሕገ-መንግሥቱ መሠረት የህዝቡን ጥያቄ በመመለስ ሃላፍነቱን ያለመወጣቱ ችግሩ ተፈትቶ በአከባቢው የሰላም አየር እንዳይነፍስ ከማድረጉም በላይ የመብት ጥሰቶች እንዲባባሱ የራሱን ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በመሆኑም እኛ በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር አባላት በዛሬው ዕለት October 17, 2020 ባደረግነው ጉባኤ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ባለ፟ 9 ነጥብ መግለጫ አውጥተናል።

1 የወላይታ ህዝብ ህግንና ስርዓትን ተከትሎ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄውን አቅርቦ በትዕግስት እየተጠባበቀ ያለውን በክልል የመደራጀት የመብት ጥያቄ በአስቸካይ ምላሽ እንዲሰጥ፤

2 የመላውን ወላይታ ህዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እያስተጋቡ በመንግስት ስራ ላይ እያሉ በሐሰት የፈጠራ ወንጀል ተጠርጥረው አለአግባብ የታሰሩ የቀድሞ ዞን አመራሮች፣ የንግዱማኅበረሰብ አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ወጣቶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤

3 በሠላማዊነቱና በጨዋነቱ የማይታማውን፣ ግዴታውንና መብቱን በማወቅ ባዶ እጁን ለሰልፍ የወጡ ንጹሀን እንዲጨፈጨፋ ባዘዙት፤ ባስፈጸሙትና በፈጸሙ የፈደራል ይሁን የክልል አመራሮች እንድሁም ያልተመጣጠነ ኃይል በተጠቀሙ የጸጥታ አካላት ላይ ተገቢው ምርመራ ተጣርቶ ለህግ እንዲቀርቡ፤

4 ያለ ጥፋታቸውና ወንጀላቸው በመንግስት ጦር ተጨፍጭፈው ህይወታቸውንና አካላቸውንላጡ ተገቢው ካሣ እንዲከፈል፤

5 የክልል መዋቅር ጥያቄ ለቅንጦት ወይም ለፉክክር አሊያም ለጥቂቶች ሥልጣንና ጥቅም ሳይሆን ለዘመናት ያለፍላጎቱ በተጫነበት ኢ-ፍትሔዊ የአስተዳደር አከላለል ምክንያት ታታሪውና ሥራ ወዳድ ህዝባችን በከፋ ድህነት ውስጥ በመሆኑ ማንነቱን፣ ባህሉንና ቋንቋውን በተገቢው ማሳደግ ባለመቻሉና በሌሎችም በርካታ ተጨባጭ ገፊ ምክያቶች መሆኑን መንግሥት በቅንነት እንዲረዳ፤

6 የህዝባቸውን ህጋዊ ጥያቄና ፍትሓዊ ትግል የደገፉ የብሔሩ ተወላጅ ምሁራንንና የመንግሥት ሰራተኞችን ከኃላፍነታቸው ማንሣት፣ ማሸማቀቅ፣ እንደዚሁም በንግዱ ማህበረሰብና በወጣቶች ላይ የሚፈጸም ወከባ፣ ጫናና ማስፈራራት በአስቸከይ እንዲቆም፤

7 የወላይታ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር መሆኑ ታውቆ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያናጋበማስመሰል በሕዝቡ ታሪክ ላይ ጥላሸት በመቀባት የሥነ ልቦና ጥቃት ለማድረስ የሚሞክሩ ኃይሎች ሁሉ ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ፤

8 የፌደሬሽን ም/ቤትም የኢትዮጵያ ብሔሮችና ህዝቦችን ያለ አድሎ በእኩል በማዬት በሕገ-መንግስቱ መስፈርት መሠረት ባጭር ጊዜ ምላሽ በመስጠት ምርጫ ቦርድ ህዝበ-ውሳኔ እንዲዘጋጅ እንዲያደርግ፤

9 በመጨረሻም መንግሥት ከሠፊው የወላይታ ህዝብ ጋር ሰላም እንዲፈጥር፣ ለዚሁም የሐገር ሽማግሌዎችን፣ የሀይማኖት መሪዎችን፤ የብሔሩ ታዋቂ ግለሰቦችንና ምሁራንን በጋራ በማወያየት መንግሥትና ህዝብ በመካከላቸው መተማመንን፤ በአከባቢው ዘላቂ ሠላምንና መረጋጋትን እንዲፈጥር በአጽንኦት እንጠይቃለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር (AWANA)

ልማታዊ ባለሀብት አቶ አበበ ዘለቀ በመሞታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

ልማታዊ ባለሀብት አቶ አበበ ዘለቀ በመሞታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

አቶ አበበ ትጉህ ሠራተኛ፣ ለሰው አሳቢ፣ ትሁትና ገር አገር ወዳድ ሰው እንደነበሩ በቅርበት የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ። አቶ አበበ ዘለቀ በወላይታ የሠሯቸው የልማት ሥራዎች የእጃቸው አሻራ ሆነው በማኅበረሰቡ ዘንድ ይኖራሉ።

አቶ አበበ በከተማዪቱ በሠሯቸው የገበያ ማዕከልና በዘመናዊ ሆቴል ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ልማታዊ ሥራዎች ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል የመፍጠር ዕቅድ እንደነበራቸው ይነገራል።

እሳቸው ቢሞቱም ታሪካቸው አይሞትም። በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማኅበር እኚህን የልማት አርበኛ ለተነጠቀው የወላይታ ማኅበረሰብ ሁሉ መጽናናትን ይመኛል።

AWANA

Dama godda (ባለዳማዉ ፈረስ) ኣቶ ኣየለ ኣዳሬ በመሞታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

Dama godda (ባለዳማዉ ፈረስ) ኣቶ ኣየለ ኣዳሬን ከልጅነቴ ጀምሮ የማዉቀዉ “ምኖ ጎባ ኣሳ” (የተሳካለት ጎበዝ ሰዉ) ተብሎ ነዉ። በዚያን ጊዜ የማዉቀዉ ግን የተዋጣለት የስራ ሰዉ መሆኑን ብቻ ሳይሆን በግርማ ሞገሱ ፈገግታዉ ቀልዱና በምክሩም ስፍራን የሚሞላ ሰዉ ነበር። ፈረንጆች “larger than life itself” የሚሉት አይነት ሰዉ።

የኣደባባይ ብቃቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ወላይታም ኢትዮጵያም ልክ እንደ ኣሁኑ ወቅት በከባድ ድባብ ዉስጥ በነበሩበት ወቅት ነበር። በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር 1984 ዓ/ም ወይም 1985 ዓ/ም ክረምት ላይ። በወላይታና አከባቢዉ በወቅት ስለነገሰዉ ዉጥረት ተነጋግሮ ዉሳኔ ላይ ለመድረስ በሶዶ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትም/ ቤት አዳራሽ ታላቅ ስብሰባ ተጠርቶ ነበር። ያኔ ወህዴድና ወህዴግ በሚባሉ የወላይታ ፓርቲዎች መካክል የነበረዉ የለየት ጦርነት የስብሰባዉ ባክግራዉንድ አካል ነበር።ነፍሱን ይማረዉና በአቶ ተፈራ መስቀሌ የሚመራዉ ወህዴድ በኢሃደግ መራሹ ፈደራል መንግስት ከፍተኛ ድጋፊ በአከባቢዉ ፖለቲካ የበላይነትን አግኝቶ ስልነበረ የስብሰባዉ አዘጋጆች እነሱ ነበሩ። ሁሉንም ሰዉ ግን ጋብዘዋል (to their credit)። Everybody who was somebody in Wolaita society የተገኘበት ይመስል ነበር። አዳራሹ አፍንጫዉ ድረስ ሞልቱል። ብዙ የፖለትካ አዋቂዎች የፓርቲ አለቆች የተማሩ ሰዎች የዚህም የዚያም ተወካዮች ብዙ ካወሩ በኋላ ከመሃክል ለአንድ የሃገር ሽማግሌ አባት ማይኩ ተሰጣቸዉ (ለአቶ አየለ አዳረ)።

የሆነ አይነት ዜማ ያለዉ በሚመስ ንግግር ለጥቂት ሰኮንዶች ማዉራት እንደጀመሩ ሰማይ ምድር ፀጥ ብሎ የሚያዳምጥ እስኪመስል አዳራሹ በታላቅ ፀጥታ አዳመጣቸዉ። ስለታሪካችን ስለአከባቢያችን ስላለፉ የሃገራችን መሪዎችም ስለጥሩነትና ክፋት በጥቂት ደቂቃዎች እጅግ ብዙ አስተማሩን። ከብዙ ምክራቸዉ ትንሽ ለማስታወስ”…ከፍ ያላችሁ ከናንተ በታች ያለዉን በጫማችሁ አትርገጡ፤ ጣቶቻቸዉን ይዛችሁ ወደላይ ሳቡዋቸዉ። ከታች ያላችሁ እናንተም ትንሽ ከፊ ያለዉን ሰዉ በክፋት መንፈስ ወደታች አትጎትቱ፤ በትከሻችሁ ወደላይ ደግፉዋቸዉ (ካፍተ)። እሶይ እሱዋ ጫዶፕተ…” ብዙ የሚስተምር ነገር ስላላቸው ስለሙሉ ታሪካቸዉ አንድ ቀን እናነብ ይሆናል።

ዳማ ጎዳ አቶ አየለ የህዝብ እንደራሴም ሆነዉ ነበር። በኋላም ከደኢህደን ካድረዎች ጋር ተጋጭተዉ ታስረዉም ነበር። በሃገር አቀፍ ደረጃ ሞደል ገበሬ ሆነዉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ ሽልማት ካገኙ ጥቅት ኢትዮዽዊያን አንዱ ነበሩ። ለአክባቢዉ ልማት ጉልህ ሚና ተጫዉተዋል። የክርስትና ህይወታቸውና የቤተሰብ አስተዳደራቸዉ በሃገር የተመሰከረላቸዉ ነበር። መጥፎ ነገርንና ክፋትን በብርቱ ይፀየፉ ነበር። ከእግዚሃብሄር በስተቀር ማንንም ሳይፈሩ እዉነት የመሰላቸዉን ነገር ድምጻቸዉን ከፍ አድርገው ሲናገሩ ኖረዋል።

ዳማ ጎዳ አቶ አየለ አዳረ ባለው አክባቢያዊ ሁኔታ ብዙ ተፅዕኖውችን ተቁዋቁመዉ ታላቅ ገድልን ተጋድለው መልካም ህይወት ኖረዉ የልጅ ልጅ አይተዉ የሰዉ ፍቅርና አክብሮት ሳይለያቸ ያረፉ ታላቅ የወላይታ ተወላጅ ኢትዮጽያዊ ነበሩ። ወደዘለአለሙ አለም ማለፋቸዉ ለርሳቸዉ እረፍት ቢኖንም ለሚዉዷቸዉ ሁኑ በስጋ ለባሽነታችን ጥልቅ ሃዘን ነዉ።
ለመላዉ ቤተሰብ ዘመድና ወዳጅ በራሴና በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆት ማህበር ስም እግዚሃብሄር ያፅናናችሁ እላለሁ።

ፕሮፌሰር ዳታ ዴአ
በሰሜን አሜሪካ የዎላይታ ተወላጆችና ወባጆች ማህበር ፕሬዚዳንት